Tuesday, June 11, 2013

ወልዲያ

ወልዲያ የሚለዉ ቃል የኦሮምኛ ሲሆን ትርጉሙ መሰባሰቢያ መገናኛ እንደ ማለት ነዉ
ከተማዋ የተቆረቆረችዉ በ 17 ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ነዉ
ከተማዋ የዕድሜ ባለፀጋ ብትሆንም የዕድገት ደረጃዋ ግን እንደ ካሮት ነዉ
ስለከተማዋ አጀማመር እና አጠቃላይ ታሪክ በሚቀጥለዉ በሰፊዉ ይጠብቁን
አሁን ላይ ከተማዋ አንዳንድ ለዉጦችን አያሳየች ትገኛለች ለምሳሌ አንዳንድ ፎቆች የከተማ ትራንስፖርት ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ይታያሉ

አለመታደል ሆኖ ከተማዋ ወላጅ አልባ ከሆነች በጣም ቆየች
በመሰረተ ልማት በኩል እሚመስሉ ነገሮች ቢኖሩም
መንገዱ ባጃጅ ማሳለፊያ ብቻ ሁኗል ከመጥበቡ የተነሳ
ሙስናዉ ተጧጥፏል
የመንገድ መብራት በታሪከ የማይበራባት ከተማ ብትኖር ወልዲያ ነች
በአሁኑ ሰአት ወጣቱ የጊዜ ማሳለፊያ ስለሌለዉ በመጠጥ በጫት በሲጋራ
በሺሻ ሱስ ዉጥ ገብተዉ ተስፋ ቆርጠው ተቀምጠዋል
ሌላውና የሚገርመው ነገር ከተማዋ ዉስጥ የጭፈራ ቤቶች በጣም ተበራክተዋል
ሃይ ባይ አተው የሴሰኛ መጠራቀሚያ ሆናለች ከተማዋ

በተጨማሪም ከተማዋ ዉስጥ በተከፈተው ዩኒቨርሲቲ ና ኮሌጅ ተማሪወች ወደ ሴተኛ አዳሪነት ተቀይረዋል
ይህ ነገር በጊዜ መላ ካልተበጀለት ወደፊት አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀርም
በሚቀጥለዉ ይጠብቁን ትዝብታችን ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment