Sunday, September 22, 2013

ኢትዮጵያዊቷ ብሩክታይት ደገፋ ለ12 ዓመታት የቆየውን የሲድኒን ማራቶን ሪከርድ በመስበር አሸነፈች

በዛሬው እለት በሲድኒ የተካሄደው ይህ የ42.2 ኪሎ ሜትር ውድድር ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2001 በአውስትራሊያዊቷ ክሪሻና ስታንቶን በ2 ሰዓት ከ38 ደቂቃ ከ11 ሰከድ ተይዞ የነበረ ሲሆን ፥ ብሩክታይት በ2 ሰዓት ከ32 ደቂቃ 45 ሰከንድ በሆነ ግዜ ነው የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ማሸነፍ የቻለችው።
በሌላ በኩል የሴቶች ግማሽ ማራቶኑን ውድድር ላውራ ጀምስ የተባለችው አውስትራሊያዊት በ1 ሰዓት 18 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት በአንደኛነት አጠናቃለች
በተመሳሳይ በተካሄደው የወንዶች የማራቶን የሩጫ ውድድር ኬንያዊው ዊሊ ኪቦር ድል የቀናው ሲሆን ፥ ኪቦር በ2 ሰዓት ከ 13 ደቂቃ 48 ሰከንድ አንደኛ ሆኖ ጨርሷል።


https://www.clickhabesh.com/~clickha1/?p=103413

No comments:

Post a Comment