Tuesday, September 24, 2013

የኬኒያ የፀጥታ ሀይል ታጋቾችንን የማስለቀቅ ዘመቻውን እያገባደደ ነው

በኬኒያ  መዲና ናይሮቢ የፀጥታ ሀይል በዌስት ጌት የገበያ ማዕከል ውስጥ በአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ ታጣቂዎች ተይዘው የሚገኙ  ታጋቾችን ለማስለቀቅ ዘመቻ እያካሄደ ነው  ።
በአሁኑ  ወቅት  የፀጥታ ሀይሎቹ የገበያ ማእከሉን  የወረሩ ሲሆን ፥  ከስፍራውም የተኩስ ድምፅ  እየተሰማ ነው ።
በዚሁ ታጋቾችን ነፃ የማውጣት ዘመቻና ታጣቂዎቹ ሙሉለሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ጥረት ገና አላለቀም፡፡
በዚህም በሃሪቱ ፖሊሶችና በአጋቾቹ መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነው ከ69 በላይ የሚሆኑ ለሞት እና ከ175 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለጉዳት መጋለጣቸውን ኬኒያ ሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡
እስከ አሁን ከተገደሉት ሁለት የካናዳና ሁለት የፈረንሳይ ዜጎች ድፕሎማቷን ጨምሮ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
የሀገሪቱ ጸጥታ ኃይል አሁንም ቀሪ አጋቾችን ለመግደል አሊያም እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ለመያዝ ጥረቱን እንደቀጠለ አስታውቋል፡፡
የአገሪቱ  ጦር  በትዊተር ገፁ  እንዳስታወቀው  እስካሁን  የተወሰኑ ታጋቾችን ፖሊስ ከታጣቂዎቹ ማስለቀቅ ችሏል ።
የአገር  ውስጥ ሚኒስቴር በበኩሉ  የፀጥታ ሀይሎቹ  ታጋቾቹን የማስለቀቁን ዘመቻ  ወደ ማጠናቀቀ  ተቃርበዋል ነው ያለው።
እስካሁን ድረስም ከሽብር ጥቃቱ ጋር በተያያዘ ለጥያቄ የሚፈለጉ 10 ተጠርጣሪዎችን መያዙንም  ጨምሮ ገልጿል። የጸጥታ ሃይሎች በበኩላቸው 3 ታጣቂዎችን መግደላቸውን እየተናገሩ ነው።
ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጥቃት ፈፃሚዎቹን መንግስታቸው የገቡበት ገብቶ እንደሚይዛቸው ተናግረዋል።
አል ሸባብ  ለጥቃቱ  ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል ።
ከከተማዋ  እየወጡ ያሉ ዘገባዎች  እንደሚያመለክቱት  እስካሁን  በሽብር ጥቃቱ 69 ዘጠኝ ሰዎች ተገድለዋል ።
በሶማሊያ  የሚገኘው የኬንያ ወታደራዊ ሀይል ጥቃትን ተከትሎ አልሸባብ በኬንያ ጥቃት ሊያደርስ እንደሚችል ለቢ ቢ ሲ መናገሩንም ዘገባው  አስታውሷል።
በደቡብ ሶማሊያ እ.እ.አ ከ2011 ጀምሮ አሸባሪውን አልሸባብ ለመምታት ከ4000 የማያንሱ የኬንያ ወታደራዊ ሀይል አባላት መሰማራታቸውንም ዘገባው አስታውሷል።
የአፍሪካ  ህብረት  ምላሽ 
የአፍሪካ  ህብረት  በሁኔታው ላይ ባወጣው መግለጫ ፥  የአልሸባብ ድርጊት በሶማሊያ የሚገኘው የህብረቱ  ጦሩ ዘመቻውን እንዲያጠናክርና የበለጠ የቡድኑ ውድቀት እንዲሰራ
የሚያደርገው ነው ብሏል ።
ህብረቱ በሶማሊያ የሚገኘው  ጦሩ  በዚያች አገር  ሰላም  እስከሚመጣ ድረስ  በዚያው  እንደሚቆይም አረጋግጧል ።

freedom4democracy

No comments:

Post a Comment