Saturday, November 2, 2013

ኬሺ ደሞዝ ደርሶታል…25 ተጫዋች አሳዉቅዋል….ጥቁሩ ኮከብ ይመጣል!


ስቲፈን ኬሺ ያለደሞዝ ለ7ወራት ሰርትዋል፤አዲስ አበባም ሲመጣ በኔፕ ነበር፤ነገር ግን በአልጣኝነት ዘመኑ በነጥብ ጨዋታ ድል አልተወሰደበትም፤ደሞዝ አልባዉ ዉጤታማ ሁንዋል፤አሁን ግን ቢያንስ ቢያንስ ዩለት ወር ደሞዙን እንደወሰደ ተሰምትዋል..ፌዴሬሽኑ በይፋ ያሳወቀዉ የተወሰነ ወራት ደሞዙን ከፍለነዋል የሚል ሲሆን አንድ የዉስጥ አዋቂ ደግሞ የ2ት ወር ነዉ የተለቀቀለት የቀረዉን ደግሞ በቅርብ ቀን ይከፈለዋል ብለዋል፤
ሰዉየዉ አሁንም ስራዉን እንደሚከፈለዉ ሰዉ እየሰራ ነዉ፤25ተጫዋቾቹን ለካላባሩ ጨዋታ ይፋ አድርግዋል፤ፕሮፌሽናሎቹ አሉበት፣፣ፌዴሬሽኑ በገንዘብ እጥረት ምክንያት መያዝ ሚችለዉ 23ት ሰዉ ብቻ ስለሆነ 2ት ተጫዋቾቹን በጊዜ ማሰናበት የደሞዝ አልባዉ ሰዉዬ ቀዳሚ ስራ ይሆናል፤4ት ሀገር በቀል ተጫዋቾቹንም ኬሺ አካትዋል፤ዝግጅቱን ከጨዋታዉ 1ሳምንት በፊት ለመጀመር እቅድ ነድፍዋል፤
በሌላ ዜና የጋና ጥቁር ከዋክብት ቡድን ለግብጽ የመልስ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ እንደሚዘጋጅ ፌዴሬሽኑ አረጋግጥዋል፤ጋናዎች ከጨዋታዉ 6ት ቀናት በፊት ሸገር እንደሚደርሱ ጨዋታዉ 1ቀን ሲቀረዉ ወደ ካይሮ እንደሚያመሩ ፌዴዉ ገልጽዋል፤ምናልባት እንደዉ ምናልባት ዋልያዉ ጋር ሊጫወቱ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል፤አዲስ አበባን የመረጡት በከፍተኛ አልቲቲዩድዋ ምክንያት እንደሆነም ተጠርጥርዋል!!ከዚህ ቀደምም ጥቁሩ ኮከብ እዚህ አዲስ አበባ ከትሞ የዝግጅት ልምምድ ማድረጉ ይታወሳል፤

 http://www.ethiotube.net

No comments:

Post a Comment