እንደማያልፍ የለም
(የካናዳው ከበደ)
አዎ፤
የኔም እምባ ፈሷል
እምነቴ ደፍርሷል
ሰበዕናየ አንሷል
ምክንያት ፍለጋ – መፍትሄ ፍለጋ
ቀኑ እስከሚጨልም – ሌሊቱ እስቲነጋ
ብቆርጥ ብቀጥል – ባነሳ ብጥለው
ዘላለም ሆነብኝ – ማለቂያ የሌለው
ሕመምሽ አሞኛል
ድካምሽ ደክሞኛል
እምባሽን ለመጥረግ – አቅም በማጣቴ
ሕሊናየ ቆስሏል – ተቃጥሏል አንጀቴ
እና….ጠንክሪ እህት ዓለም
ይሄም ቀን ይረሳል – እንደማያልፍ የለም
https://www.goolgule.com
No comments:
Post a Comment