Wednesday, October 30, 2013

Reshuffles within the ENDF የሰሜን ዕዝና የአየር ኃይል ዋና አዛዦች በሌሎች ተተኩ

594x251xTPLF-generals_jpg_pagespeed_ic_3hefVwMBZp
October 30, 2013
The Ethiopian National Defense Force (ENDF) has reshuffled at least two of its long serving top commanders. Both commanders were former gurriella fighters and current members of the core member party of the ruling Front, EPRDF, the Tigre People’s Liberation Front (TPLF). According to the Addis Abeba based Amharic biweekly, Reporter, Lieutenant General Se’are Mekonen, Commander of the Northern Command since 1998 and Major General Mola Hailemariam, Head of the Ethiopian Air Force, have both been removed from their posts and ”brought in to the center for a better appointment and responsibilities”. Major General Yohannes Woldegiorgis, who has been heading the Ethiopian force in Somalia, has now become the Head of the Northern Command replacing Se’are. Mola was replaced by Major General Adem Mohammed. All the appointees come from the same Front, TPLF. Other reshuffles and reappointment have also been made.
-የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ
በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ፡፡
በሽግሽጉ መሠረት ኤርትራ ኢትዮጵያን ከወረረች ጀምሮ የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ታዋቂው ሌተና ጄኔራል ሰአረ መኮንን በተሻለ ኃላፊነት ወደ ማዕከል እንዲመለሱ መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በተለይም የኤርትራን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የመከታተልና የመመከት ኃላፊነት በተሰጠው የመከላከያ ሠራዊቱ የሰሜን ዕዝ አወቃቀር ላይ ማሻሻያ መደረጉን ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ በተደረገው ማሻሻያ መሠረት የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ የነበሩት ሌተና ጄኔራል ሰአረ ወደ ማዕከል እንዲመለሱ ሲደረግ፣ በምትካቸው ሜጀር ጄኔራል ዮሐንስ ወልደ ጊዮርጊስ ተሹመዋል፡፡ ሶማሊያ የዘመተውን ሠራዊት የመሩና በተለያዩ ኃላፊነቶች የሠሩ መሆኑ ታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጄኔራል ሞላ ኃይለ ማርያም ምትክ ሜጀር ጄኔራል አደም መሐመድ መተካታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ሜጀር ጄኔራል አደም በአየር ኃይል አብራሪነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በመከላከያ ሠራዊት የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ደግሞ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት የአቢዬ ግዛት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ምክትል አዛዥ የነበሩ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር በሌሎች ጄኔራል መኮንኖች ኃላፊነቶች ላይም ሽግሽግ ማድረጉን የገለጹት ምንጮች፣ ከአየር ኃይል አዛዥነታቸው የተነሱት ሜጀር ጄኔራል ሞላ እንደ ሌተና ጄኔራል ሰአረ ወደ ማዕከል ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት መሾማቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ላለፉት አሥር ዓመታት በላይና በአሁኑ ወቅትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ የጠቅላይ ማኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሕግና ፍትሕ አስተዳደር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ተሹመዋል፡፡
አቶ አስመላሽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንባር ቀደም የሥራ ኃላፊነት በሆነው የሕግ ማውጣት ተግባር በስተጀርባ ቁልፍ ከሚባሉት ግለሰቦች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ባገኙት የሕዝብ ውክልና ባሳለፏቸው በርካታ ዓመታት የምክር ቤቱ የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
የሚመሩት ቋሚ ኮሚቴ ለፓርላማው የሚቀርቡ ረቂቅ ሕጐችን በተለይም ሕግና አስተዳደርን የተመለከቱትን በዋናነት የሚመለከት ሲሆን፣ የአገሪቱ የሕግና የፍትሕ ሥርዓት የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማትንም የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት አለው፡፡
በቅርቡ በአቅም ማነስ ምክንያት ከኃላፊነት የተነሱት የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ ከመሰናበታቸው አንድ ቀን በፊት ለፓርላማው ያቀረቡትን ሪፖርት በመተቸትና የሚኒስቴሩን ጉድለቶች በማስረዳት እንዲያስተካክሉ አቶ አስመላሽ መመርያ መስጠታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ethiopianreporter

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቋመ፤ የዕጩዎችን ዝርዝር ለርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ ያቀርባል


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው፣ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ዘጠነኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው የኤጲስ ቆጶሳትን ምርጫ የሚያስፈጽም አስመራጭ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት ሲኾን የትግራይ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ኦሮሚያ አህጉረ ስብከትን በመወከል የተመረጡ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት÷ ከትግራይ ብፁዕ አቡነ፣ ከወሎ የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ከጎንደር የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ከጎጃም የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ከኦሮሚያ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ – ወሊሶ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአስመራጭ ኮሚቴ አባልነት ተሠይመዋል፡፡
ዕጩዎች በሕገ ቤተ ክርስቲያን ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በወጣው መስፈርት ብቻና ብቻ ለይቶ እንዲያቀርብ በምልአተ ጉባኤው ከባድ አደራ የተጣለበት አስመራጭ ኮሚቴው÷ ከመስፈርቱ ውጭ ጎጠኝነትን ጨምሮ በተለያዩ መደለያዎች ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነትን ለማግኘት ካሰፈሰፉ ቆሞሳት እንዲጠበቅ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው በመምረጫ መስፈርቱ መሠረት የዕጩዎችን ማንነት ከመለየት ባሻገር ከበጀት፣ ከመንበረ ጵጵስና እና ከጽ/ቤቶች መማሏት አኳያ ኤጲስ ቆጶሳቱ ሊመደቡባቸው የሚገቡ አህጉረ ስብከትን በቅደም ተከተል በመለየት ብዛታቸውን የመወሰን ሥራም እንደሚሠራ ተገልጧል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው ሥራውን ጨርሶ ሪፖርቱን የሚያቀርበው ለመጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሲኾን ሥርዐተ ሢመቱም የምልአተ ጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎ እንደሚፈጸም ተመልክቷል፡፡
የኤጲስ ቆጶሳትን ምርጫና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ ሌሎች መረጃዎችን ወደፊት እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡

haratewahido

Tuesday, October 29, 2013

ሰበር ዜና – የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ላይ መነጋገር ጀመረ – በገዳማዊ ሕይወት ያልተፈተኑ፣ በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድ የወደቁ፣ በፍቅረ ንዋይ እና በፍቅረ ሢመት ያበዱ፣ የውድቀት ታሪክ የሞላቸው፣ በውጭ ባሉ ሰዎች ክሥና ስሞታ እንጂ መልካም ምስክር የማይሰማባቸው፣ በአገልግሎት ያልተፈተኑ ሰዎችን መሾም አደጋው የበዛ ነው!!



  • ምልአተ ጉባኤው አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሠይም ይጠበቃል፤ አስመራጭ ኮሚቴው ተሿሚ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳትን ይጠቁማል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፲፰ በተደነገገው መሠረት በአስመራጭ ኮሚቴው በዕጩነት ተመርጠው ከቀረቡት ቆሞሳት መካከል በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፭ ቁጥር ፺ – ፺፭ እንደታዘዘው ተሿሚ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በድምፅ ብልጫ ይመረጣሉ፤ ተወዳዳሪዎች ያገኙት ድምፅ እኩል ከኾነ ዕጣ የወጣለት ቆሞስ ኤጲስ ቆጶስ ኾኖ ይሾማል፡፡
  • በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ተቀብተው የሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት የሚመደቡባቸው ዐሥር አህጉረ ስብከት÷ ሽሬ እንዳሥላሴ፣ አክሱም፣ ዋግ ኽምራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ፣ ዳውሮ፣ ጉራጌ፣ ጉጂ ቦረና እና ጅጅጋ እንደሚኾኑ ይጠበቃል፡፡ በአንድ ቤተ ጉባኤ/የአብነት ትምህርት/ ምስክርነት ማግኘትና የሚሾሙበትን ሀ/ስብከት አካባቢ ቋንቋ መናገር መሠረታዊ የመምረጫ መስፈርቶች እንደሚኾን ይጠበቃሉ፡፡
  • የኤጲስ ቆጶሳቱ ጥቆማና ምርጫ በተሻሻለው ሕገ ቤተ ክርስቲያን የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሕግ መሠረት እንደሚከናወን ቢጠቆምም በፍትሕ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት እንደተመለከተው የምርጫው ሂደት ግልጽነት የጎደለውና በከፍተኛ ምስጢር የተያዘ መኾኑ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፡፡

*      *      *

  • በፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት መሠረት ለኤጲስ ቆጶስነት ከፍተኛ መዓርገ ክህነት የሚበቃ ቆሞስ አባት÷ የሐዋርያነት ምልክት ያለው፣ በዚህ ዓለ ክርስቶስን ተክቶ የሚሠራ ክርስቶስን በግብር የሚመስል የክርስቶስ እንደራሴ ነው፡፡ በሥጋዊና መንፈሳዊ ተክለ ሰብእናው ነውር የሌለበት፣ ልቡናው ከሐኬት የራቀ፣ ድንግላዊ ኾኖ ሥርዐተ ምንኩስና የፈጸመ፣ በትምህርቱ ብሉይ እና ሐዲስ ኪዳናትን የተማረና የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ ሒደት በመረዳት ከፍተኛ ችሎታ ያለው፣ በጠባዕዩ የተመሰገነና ሙሉ አካል ያለው ጤናማ ሰው መኾን ይጠበቅበታል፡
  • ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟላ ቆሞስ ሲገኝ ኤጲስ ቆጶስነት የሚሾመው፣ በሚሾምበት ሀገረ ስብከት የሚገኙ ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የኾናቸው ካህናትና ምእመናን ሲመርጡት፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሲፈቅዱ ነው፡፡
  • ማኅበረ ካህናትና ምእመናን በኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾምላቸው ስለመረጡት አባት ደግነት፣ ትሩፋት፣ ንጽሕና እና ከነውር የራቀ ስለመኾኑ እማኝነታቸውን ወይም ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ይጠየቃሉ፡፡ ጌታችን ቅ/ጴጥሮስን ‹‹ትወደኛለኽ›› እያለ ሦስት ጊዜ መልሶ መላልሶ እንደጠየቀው፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሦስት ጊዜ እየመላለሰ ምእመናኑንና ካህናቱን ማረጋገጫ ይጠይቃቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እጃቸውን አንሥተው ‹‹የሚገባው ነው›› እያሉ ሦስት ጊዜ መልስ ይሰጣሉ፤ ያረጋግጣሉ፡፡ በዚህ መልኩ ማኅበረ ካህናቱና ሕዝበ ክርስቲያኑ እየመሰከረላቸው ይሾማሉ፡፡ ካህናቱም ሕዝቡም በሙሉ ስለ ሢመቱ ምስክር ኾነው ይቀመጣሉ፡፡
  • ክርስቶስ ‹‹እናንተን የተቀበለ እኔን ይቀበላል›› ያላቸው የቅዱሳን ሐዋርያት ተከታይና በክብራቸው የቅዱሳን ሐዋርያት አምሳያ የኾኑ ኤጲስ ቆጶሳት÷ በመዓልትም በሌሊትም ስለ ራሳቸውና ስለ ሕዝቡ ስለ ሀገሩ ስለ ዓለሙ ይጸልዩ ዘንድ ታዝዘዋል፤ ንቁሐን ትጉሃን ኾነው ኦሪትን፣ ነቢያትን፣ ወንጌልን፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ምዕራፉን ቁጥሩን አንቀጹን እየለዩ ይተረጉሙና ያስተምሩ ዘንድ ይገባቸዋል፡፡ ነቢዩ ሆሴዕ ‹‹መምህሩ ደግ ከኾነ ሕዝቡም እንደርሱ ደጋግ ይኾናሉ›› እንዳለው ሕዝብን በምሳሌነት በማስተማር የሚተጉ፣ ሁሉንም ጾታ ምእመናንን የሚወዱ፣ ቂም በቀል የማይዙ፣ ኀዳጌያነ በቀልና ልበ ሰፊዎች ነገር አላፊዎች መኾን አለባቸው፡፡
  • ከአጻዌ ኆኅት እስከ ቅስና ያለውን ሥልጣን ይሰጣሉ፤ እንደ ጥፋታቸው መጠን መቅጣት፣ ከሥልጣን መሻር፣ ከአገልግሎት ማሰናበትና ማገድ ይችላሉ፤ በኃጢአት የታሰረውን በሀብተ ክህነታቸው ይፈታሉ፤ ሥጋወደሙን ለምእመናን ያቀብላሉ፡፡
  • ኤጲስ ቆጶሳት በተመደቡበት ሀ/ስብከት ስማቸው ዘወትር በጸሎት ጊዜ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ (ፓትርያርኩ) ቀጥሎ ይጠራል፡፡ ያለበቂ አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ምክንያት ኤጲስ ቆጶሳት አንዴ ከተመደቡበት ሀገረ ስብከት አይነሡም፡፡ ኤጲስ ቆጶሳትን ያለበቂና አስገዳጅ ምክንያት ከሀገረ ስብከታቸው ማንሣት ባልን ከሚስት እንደማፋታት ይቆጠራል፡፡
  • ምእመናን በየሀገረ ስብከታቸው የሚሾሙ ኤጲስ ቆጶሳትን ሊወዷቸው፣ ሊያከብሯቸው፣ ሊታዘዙላቸው፣ በማንኛውም ሃይማኖታዊ ጉዳይ ተገቢ በኾነ መንገድ ሊደግፏቸው ይገባል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን በምእመናንና በካህናት ጉባኤ ጥቆማ በአገልግሎት ብቃታቸው ተመስክሮላቸው የሚሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት ከመንበር የሚወርዱት ከሥልጣን የሚሻሩት በሞት ሲለዩና የሃይማኖት ሕፀፅ ሲገኝባቸው ብቻ ነው፡፡
  • እንደ ጥንቱ ሥርዐት ከኾነ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት መዓርገ ክህነት የሚሰጠው በአብዛኛው ትሩፋትን፣ አገልግሎትን፣ ቅድስናን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አባቶች ያኖሩትን ትምህርት በመጣስ አንድ ሰው አምኛለኹ፤ በቅቻለኹ ብሎ ቢቀርብ እንኳ ቤተ ክርስቲያን መሾም የለባትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መዓርግ በታማኝነት ሊያገልግሏት የሚችሉትን አገልጋዮች በጥንቃቄ መምረጥ አለባት፡፡
  • የአበውን ትውፊት በመጣስ የዕድሜንና የአገልግሎትን ኹኔታ ግምት ውስጥ ሳያስገቡ ቢሾሙ በዲያቢሎስ ሽንገላ በትዕቢት እየተነፉ እነርሱም ሳይገለገሉ ቤተ ክርስቲያንንም ሳያገለግሉ የጥፋት መሣርያ ይኾናሉ፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያንን ሥሯን መሠረቷን የሚያውቁ፣ በገድልና በትሩፋት፣ በትምህርትና በቅድስና ሕይወት ጸንተው የኖሩትን አባቶች ከገዳማት ጭምር እየፈለገች መሾም ይጠበቅባታል፡፡ በቅድስናቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች መሾም በእውነት ምእመናንን በጸሎታቸው የቅድስና ሕይወታቸው ተካፋይ ያደርጋቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በአግባቡ ያላገለገሉ፣ በገዳማዊ ሕይወት ያልተፈተኑ ሰዎችን ያለምንም መስፈርት መሾም ሐዋርያው እንደተናገረው በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድ ይወድቃሉ፤ አደጋውም የበዛ ሊኾን ይችላል፡፡
  •  ewunet.blogspot.com

ሠላይና ተሠላይ፤ ወዳጅና ጠላት


አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።
ARCHIV - US-Präsident Barack Obama und Bundeskanzlerin Angela Merkel unterhalten sich am 18.06.2012 in Los Cabos, Mexiko, beim Familienfoto. Merkel setzt bei der Aufklärung der millionenfachen Datensammlung des Geheimdienstes NSA nun auf eine Reise von Vertretern der Bundesregierung und deutscher Geheimdienste in der nächsten Woche nach Washington. Foto: Peer Grimm dpa (zu dpa Merkel verspricht größtmögliche Offenheit bei US-Ausspähaffäre vom 05.07.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ወዳጁ ናቸዉ
ለካሳትሮ፥ ለብሬዥነቭ፥ ለማኦ፥ ለ ደጎል፥ ለንጎ በርግጥ አዲስ አልነበረም።አይደለምም።የኤንርኮ ፔና ኔቶ ኢሜል መጠለፍ- ጉድ አሰኝቶ ነበር።የዲልማ ሮሴፍ-ኢሜል መጠለፍ-አስደንቆ ነበር።የሜርክል ሥልክ መጠለፍስ? ጉዱን ጉድ ዘለቀዉ-እንበል ይሆን።የስላላዉ ቅሌት መነሻ፥ዳራዉ ማጣቃሻ፥ የፖለቲካዉ እድምታዉ መድረሻችን ነዉ-ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።

ሚዚያ ሃያ-አንድ 1943 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።) ፈረንሳይን ከናዚ ጀርመኖች አገዛዝ ነፃ ለማዉጣት የሚዋጋዉ ጦር አዛዥ ጄኔራል ሻርል ደጎል የነፃዋ ፈረንሳይ ባሕር ሐይል ጦርን ለመጎብኘት ከተጠጉባት ብሪታንያ በብሪታንያ አዉሮፕላን ተሳፈሩ።ቆፍጣናዉ፥ ቁጡዉ፥ እልሐኛዉ ረጅሙ ጄኔራል ከትንሿ አዉሮፕላን እንደተሳፈሩ አብራሪዉ (ፓይለቱ) አዉሮፕላንኗን እንደማስነሳት ትንሽ አንገጫገጨና ወዲዚያዉ አቆማት።ጉዞዉ ተዘረዘ።

አዉሮፕላንኗ ስትፈተሽ የሞተሯ አካል በአሲድ መበላሸቱ ታወቀ።አሲዱን አዉሮፕላንዋ አካል ላይ የረጨዉ ወገን ማንነት-እስካሁን ሚስጥር ነዉ።ጄኔራሉ ግን ያኔዉኑ «የብሪታንያ ሰላዮች ሻጥር» ለማለት አላመነቱም።የአዉሮጳ እብሪተኞች የለኮሱት ጦርነት ዓለምን በሚያነድበት በዚያ ዘመን ወዳጅን ከጠላት መለየቱ-ከባድ ነበር።በዚሕም ሰበብ ደ ጎል እንደጠረጠሩት ብሪታንያዎች አድርገዉት ከነበር-ብዙዎችን ብዙም አላስደነቀም ነበር።
ARCHIV - US-Präsident Barack Obama (r) wischt sich am 19.06.2013 den Schweiß von der Stirn neben Kanzlerin Angela Merkel auf einem Podium vor dem Brandenburger Tor am Pariser Platz in Berlin. Foto: Marcus Brandt/dpa (zu dpa Obama war angeblich in NSA-Abhörattacken gegen Merkel eingeweiht vom 27.10.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++ ተሠላይና አሰላይ


ከብዙ አመታት በሕዋላ የደጎልን ቤተ-መንግሥት የተረኩቡት ፕሬዝዳት ኒኮላ ሳርኮዚ ከጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ከወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጋር የነበራቸዉ ግንኙነት ከመሪዎች-ወዳጅነትም ጠንከር፥ ጠለቅ ያለ-ነበር ይባላል።ሳርኮዚ ከሜርክል ጋር ሥላላቸዉ ግንኙነት ሥለሚያደርጉት ዉይይት ሲጠየቁ፥«ሁሌ እንገናኛለን፥ በስልክ፥ እንነጋገር፥ ኤስ ኤም ኤስ እንለዋወጣለንም» እያሉ የግንኙነት ዉይይታቸዉ ደረጃ ዘርዝረዉ ነበር።

የሜርክል መልዕክት ከሳርኮዚ አይን-ጆሮ በሚደርስበት ፍጥነት ከአሜሪካ ሰላዮች ኮምፒዉተር ላይ ይዘረገፍ ነበር።ይሕን በርግጥ ሳርኮዚም፥ ሜርክልም ከኛ እኩል ያወቁት ሰሞኑን ነዉ።NSA በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የአሜሪካ ብሔራዊ የሥለላ ድርጅት ባልደረባ የነበሩት ቶማስ ድራክ እንደሚሉት ሜርክልን መሠለል ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን መጣስ ነዉ።

«ይሕ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ክፉኛ መጣስ ነዉ።ይሕ ለመራሒተ-መንግሥት ሜርክል የግል ጉዳይ ነዉ።የግላቸዉ ተንቀሳቃሽ ሥልክ ነዉ።(ያን መጥለፍ) ለምን አስፈለገ።ከእዉነኛ ጠላትሕ ጋር በምታደርገዉ ዉጊያ የቅርብ ተባባሪሕን?»

ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፥ ዓለም አቀፍ ሕግ በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት ነበር።ዛሬም አለ።አንዴም ግን ተከብሮ አያዉቅም።ሕግ፥ ደንብ፥ ሥምምነቱን የሚጥሰዉ ደግሞ ሕግ-ደንቡን ካወጣዉ፥ አስከብረዋለሁ ከሚለዉ ሐያል ዓለም ሌላ ማንም አይደለም።
በቀዝቃዉ ጦርነት ወቅት ልክ እንደ ዓለም አቀፉ ሕግ ደንብ ሁሉ የሞስኮ፥ ቤጂንግ ተባባሪዎች፥ የለንደን-ዋሽግተን፥የቦን ፓሪስ ተሻራኪዎች ጎራ ለይተዉ አንዱ የሌላዉን ሚስጥር ማጭለጉ የፖለቲካዉ ፈሊጥ፥ የስለላዉ ወግ ነበር።

የሐገር መሪዎችን እንቅስቃሴ መከታተል አይደለም መግደል ማስገደልም የፖለቲካ መርሕን የማጠናከር፥ ርዕዮተ-ዓለምን የማዳን-ማስፋፋት ሥልት አካል ነበር።የአሜሪካዉ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት CIA ሹም ኮሎኔል ጄ ሲ ኪንግ የኩባዉን ኮሚንስታዊ መሪ ፊደል ካስትሮ-ከማስገደል ሌላ ሌላ አመራጭ እንደለሌ የጠቆሙት በ1959 ነበር።

ያኔ ዓለም አቀፍ ማሕበር ዲፕሎማሲ፥ ሕግም ነበር።ዲፕሎማሲ ሕግ፥ ደንቡ የሚረቀቅ፥ የሚወሰን የሚበየነዉ ደግሞ ከኒዮርክ ነበር፥ ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ።የአሜሪካዊ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት CIA ካስትሮን ለማስገደል ስድስት መቶ ሰላሳ-ስምንት ጊዜ ያደረገዉ ወይም አድርጓል የተባለዉ ሙከራ የብዙ መፅሐፍት፥ የዝነኛ ፊልም ርዕሥም ሆኗል።

አያቱላሆች የቴሕራንን ቤተ-መንግሥት ከተቆጣጠሩበት ከ1979 ጀምሮ ኢራን የእስራኤልም፥ የአሜሪካኖችም አሜሪካኖችን የሚመሩት የምዕራቡ ዓለምም ቀንደኛ ጠላት ናት።በሕዝብ የተመረጡት የኢራን ጠቅላይ ሚንስትር መሐመድ ሞስዳቅሕን በ1953 ከስልጣን ያስወገደዉ ማን ነበር? ፓትሪስ ሉምባ እንዴት-እና ማን ገደላቸዉ።ራፋኤል ሊኒዳስ ትሩሔሎስ፥ ንጎ ዲንሕ ዲየምንስ?
US-Bürger demonstrieren am 24.10.2013 nahe dem Kapitol in Washington DC gegen die Überwachung durch Geheimdienste wie die NSA. (Foto: Monika Griebeler / DW) - eingestellt von Andreas Grigo ተቃዉሞ


ጥያቄዉ-ጥያቄ ይወልዳል እንጂ ማብቂያ የለዉም።ዓለምን የሚመራዉ ግን ዓለም አቀፉ ሕግ ዲፕሎማሲ ሳይሆን የሐያላን ፍላጎትና ፍቃድ መሆኑ ሐቅ ነዉ።የሐያላኑን ፍላጎት ለማስከበር ደግሞ በግልፅ የሚታወቀዉ ሐያላኑ ወዳጅ ከሚሉት ጋር መተባበር መሻረክ መወዳጀታቸዉ ነበር።እስከ 2007 ድረስ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የስለላ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር የነበሩት ፔተ ሆክስትራ እንደሚሉት ግን በስለላዉ ዓለም ከወዳጅም-መሐል ተጠርጣሪ ወዳጅ አለ።

«ይሕ ሊሆን የሚችል ይመስለኛል።በስለላዉ ዓለም ፈረንሳዮች፥ ጀርመኖች፥ እስራኤሎች አሜሪካኖች ሁላችንም ጥሩ ወዳጆች ነን።ግን አንዳችን ሌላችንን የምንሠልልበት ጊዜ ሊኖርም ይችላል-የሚል መግባባት ያለ ይመስለኛል።ይሕ (በሰላዮች ዘንድ) በጣም በጣም የታወቀ ነዉ።»

ኮሚንስቶች የሐቫና፥ የሳንዲያጎ፥ የማናጉዋ የሌሎችንም የደቡብ አሜሪካ ሐገራት አብያተ-መንግሥታትን ሲቆጣጠሩ ወይም ለመቆጣጠር ሲያሰጉ የዩናይትድ ስቴትስዋ የቅርብ ጎረቤት፥ ታማኝ፥ ታዛዥነቷን አጓድላ አታዉቅም።ሜክሲኮ።

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት በሕዋላ እነ-ሑጎ ሻቬዝ አሜሪካኖችን የሚቃወም ግንባር ለመፍጠር ሲፍጨረጨሩም ያቺ-የአሜሪካ የቅርብ ጎረቤት በታማኝ ታዛዥነቷ እንደፀናች ነበር።ነዉም።ኤንሪክ ፔና ኒቶ ለፕሬዝዳትነት ሲወዳደሩ-ሲመረጡም እንደ ብዙ ቀዳሚዎቻቸዉ ሁሉ ለሐያል፥ ሐብታም፥ ታላቅ ጎረቤታቸዉ ታማኝ ታዥነታቸዉን እንደጠበቁ ነዉ።

በእጩነት ከተመዘገቡ ጀምሮ በምርጫዉ ካሸነፉ-ለሚንስትርነት የሚሾሙ የሚሽሩትን ፖለቲከኛ ስብዕና ማንነት፥ የሚዘረዝር፥ የምርጫ ዘመቻቸዉን ሥልት የሚያትት መልዕክት ለወዳጅ ተከታዮቻቸዉ ኢሜይል ይፅፋሉ። የNSA ሰላዮች ዋሽግተን ቁጭ ብለዉ የሜክሲኮዉን ፕሬዝዳት ኢሜይል ከፕሬዝዳንቱ ደጋፊ፥ተከታዮች እኩል ያነቡ ነበር።የብራዚሏ ፕሬዝዳት የወይዘሮ ዲልማ ሮሴፍ ኢሜዬልም-እንደዚያዉ ነዉ።

አሜሪካዊዉ ሠላይ ኤድዋርድ ስኖደን ሐገር መስሪያ ቤቱን ክዶ ከኮበለለ ወዲሕ የማይሰማ ጉድ የለም።አንዳድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት የሶቬት ሕብረት ኮሚንስቶች በስታሊን ዘመን የሶቬት ሕብረት ሕዝብ ከሚሠልሉት በላይ የአሜሪካ መንግሥት አሜሪካዉያንን ይሰልላል።ለአሜሪካ ሕዝብ ያልራራ ሥርዓት የፈረንሳይ ኩባንያዮችን፥ የስጳኝ ፖለቲከኞችን፥ የዓለምን ሕዝብ የሜክሲኮ፥ የብራዚል፥ የሌሎች ከሰላሳ በላይ መሪዎችን ቢሰልል-በርግጥ ሊያስደንቅ አይገባም።

ያምሆኖ የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት የሥልክ መልዕክት መጠለፉን ከአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት እስከ ሩሲያ መሪዎች ተቃዉመዋል።የጀርመን ፖለቲከኞች የሜርክል ደጋፊም ሆኑ ተቃዋሚዎችም እኩል አዉግዘዉታል።

«እንደሚመስለኝ ይሕ በጀርመን-አሜሪካኖችን ግንኙነት ያለዉን መተማመን ክፉኛ የሚጎዳ ነዉ።መተማመኑ ዳግም ሊገነባ የሚችለዉ እዉነታዉ በግልፅ ወጥቶ ማየን ከቻልን በኋላ ነዉ።

ይላሉ፥-የዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የSPD የምክር ቤት እንደራሴዎች አስተባባሪ ቶማስ ኦፐርማን ።ሥለ ጀርመን እና ጀርመንን የሚመለከቱ መረጃዎችን የመሰብሰብ መከታተሉ ሐላፊነት የጀርመን የሥለላ ድርጅት ነዉ።ቡንደስ ናሕሪሽተን ዲንስት።BND በጀርመንኛ ምሕፃሩ። የስለላዉን ድርጅት በበላይነት የሚያስተዳድርና የሚመራዉ ደግሞ የጀርመን ፌደራዊ የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ነዉ።

የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሐንስ ፔተር ፍሬድሪሽ ግን የመሪያቸዉን መሰለል እንደማንኛዉም ሰዉ ከመገናኛ ዘዴዎች የሰሙ ያክል ነዉ-የተቆጡት።

«ከአሜሪካኖች ጋር በዚሕ ሁኔታ አንሰራም።መተማመኑ ተበላሽቷል።እና እንደሚመስለኝ የተበላሸዉን መተማመን ለመጠገን ሁነኛ እርምጃ መወሰድ አለበት።»

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።

«የዋሕነት ይመስለኛል።የጀርመን መንግሥት (ባለሥልጣናት) በወዳጆቻቸዉ ሊሰለሉ እንደሚችሉ ማወቅ ነበረባቸዉ።ነገሩ ከተፈፀመ አስደናቂዉ ነገር የሚመስለኝ፥ (ሥለላዉን) ለማስቆም የጀርመን የስለላ ማሕበረሰብ አስፈላጊዉ አፀፋ-እርምጃ አለመዉሰዱ ነዉ።»

Titel: Demonstration #stopwatchingus gegen NSA und Überwachung in Washington, DC, USA
Schlagworte: NSA, Überwachung, Demonstration, stopwatchingus
Wer hat das Bild gemacht?: Monika Griebeler
Wann wurde das Bild gemacht?: 26.10.2013
Wo wurde das Bild aufgenommen?: Washington, DC, USA
ተቃዉሞ
የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ስልክ መጠለፉ-መሰላላቸዉም እርግጥ ነዉ።ሜርክል መሰለላቸዉን ፕሬዝዳት ባራክ ኦቦማ ያዉቃሉ-አያዉቁም እያነጋገረ ነዉ።ካወቁ ከመቼ ጀምሮ የሚለዉም ያጠያይቃል። እራሳቸዉ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳት ፍራንሷ ኦሎንድ የአዉሮጳ ሕብረት ወክለዉ ለኦባማ አቤቱታ ያቀርባሉ። ወደ አንድ ሺሕ የተገመቱ አሜሪካኖች በመንግሥታቸዉ መሠለላቸዉን በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል።አቤቱታ፥ ተቃዉሞ፥ ዉግዘት፥ ሰልፉ ምናልባት ይቀጥል ይሆናል፥ መሳለል-መጠላለፉ ያስቆመዋል ባይ ግን የለም።ምክንያት፥-ድሮ እንዲያ ነበር፥ ዛሬ እንዲያ ነዉ።ነገም።በዚሕ ዝግጅት ላይ ያላችሁን አስተያየት ላኩል። ማሕደረ ዜና ቢቃኘዉ ጥሩ ነዉ ብላችሁ የምትገምቱትን ወቅታዊ፥ ብሔራዊ፥ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ በተለመደዉ አድራሻችን ጠቁሙን።ለዛሬዉ ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰመን።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

dw.de

Monday, October 28, 2013

“መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ

በመልካሙ ተክሌ
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 16 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ  ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም  ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ” በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ፣ በርካታ ጳጳሳት ተሳትፈውበታል፡፡ መጽሐፉ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየታተመ ሲሆን በዚህ ሳምንት ከተጠናቀቀ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ሊመረቅ እንደሚችል ታውቋል፡፡ 

http://www.andadirgen.org/2013/10/blog-post_27.html

Saturday, October 26, 2013

በሣኡዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ ነን አሉ


Written by አለማየሁ አንበሴ
የመኖሪያ ፍቃድ ሳያገኙ በሳውዲ አረቢያ በጥገኝነት ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን የሃገሪቱ መንግስት በሰጣቸው የ5 ወራት የምህረት ጊዜ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን የዜግነት ማረጋገጫና ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በሃገሪቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊፈፀምላቸው ባለመቻሉና የጊዜ ገደቡም በመጠናቀቁ ከሀገሪቱ ሊባረሩ እንደሚችሉ ምንጮች ገለፁ፡፡
የሳውዲ መንግስት ህገወጥ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣውን መስፈርት ለሚያሟሉ ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት ያስቀመጠው የተራዘመ የምህረት አዋጅ ጥቅምት 24 ቀን 2006 የሚጠናቀቅ ሲሆን ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ በርካታ ኢትዮጵያውያን የህጋዊ ዜግነት ማረጋገጫና ፓስፖርት ለመስጠት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለመተባበሩ በጭንቀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ በጂዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጠየቀው መሠረት ማረጋገጫውን ቢያቀርቡም “ፓስፖርት ሃገር ቤት ተሠርቶ እስኪመጣ ጠብቁ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው የሚገልፁት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ በተጓተተው የኤምባሲው አሠራር ምክንያት በሃገሪቱ የመኖር ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል፡፡ የሃገሪቱ መንግስት ቀደም ሲል ያወጣውን አዋጅ ሽሮ የ5 ወራት የምህረት ጊዜ መስጠቱ የሚመሰገን ነው ያሉት ኢትዮጵያውያኑ፤ የሌሎች ሀገራት ዜጐች የተሰጣቸው ተመሳሳይ እድል እንዳይበላሽባቸው ኤምባሲዎቻቸው ባደረጉላቸው ትብብር የሚፈለገውን የመኖሪያ ፍቃድ ማውጣት እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡
ኤምባሲው ለስራው መጓተት “በቂ የሰው ሃይል የለኝም” የሚል ምክንያት ማቅረቡን የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ “በሃቀኝነት ለዜጐቹ የሚያስብ ኤምባሲ ቢሆን ኖሮ ከሃገር ቤትም ቢሆን የሰው ሃይል በመጨመር እድላችን እንዳይበላሽ መጣር ይችል ነበር ብለዋል፡፡
የተራዘመው የጊዜ ገደብ እየተገባደደ ባለበት ወቅትም የሃገሪቱ መንግስት መስፈርቱን አሟልተው ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያልተቀበሉትንም ሆነ ያስጠጓቸውን እንደሚቀጣ እያስጠነቀቀ መሆኑን የዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
በጂዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አንድ ዲፕሎማት ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ የፓስፖርት ጉዳይ ከደህንነት ጋር የሚያያዝ እና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን አመልክተው፤ ዜጐች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እስካቀረቡ ድረስ ፓስፖርት የማያገኙበት ምክንያት እንደሌለ መግለፃቸው ተመልክቷል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ አድማስ በስልክ ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውን በሣውዲ የኢትዮጵያ ኤምባሲን ማነጋገር የተሻለ እንደነበር አመልክተው “የኤምባሲው ዋነኛ ተልእኮ ዜጐችን ማገልገል ነው፣ ስለዚህ ለዜጐች ጥቅም ምንጊዜም መቆምና መስራት አለበት” ብለዋል፡፡ አክለውም እንዲህ ያለ ቅሬታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማመልከት ይችላሉ ብለዋል፡፡
Source-www.addisadmass.com

ሁለት አሜሪካዊያን መርከበኞች በናይጄሪያ የባህር ዳርቻ በወንበዴዎች ታገቱ

ሁለት አሜሪካዊያን መርከበኞች በናይጄሪያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ወንበዴዎች ታገቱ።
ወንበዴዎቹ በመርከቧ ላይ በሰነዘሩት ጥቃት ቀድመው ንብረትነቷ የአሜሪካ የሆነችውን መርከብና 11 ተጨማሪ መርከበኞችንም አግተው የነበረ ቢሆንም ፤ ወዲያውኑ መልቀቃቸው ተሰምቷል።
ወንበዴዎቹ አግተዋቸዋል የተባሉትን ሁለት መርከበኞችን ግን ወደ ናይጄሪያ የባህር ዳርቻዎች ወስደዋቸዋል።
መረጃው የደረሰው የናይጄሪያ የባህር ሃይልም ታጋቾችን ለማዳን ሃይሉን ወደ ስፍራው እንዲሰማራ ነው ትእዛዝ ያስተላለፈው።
ምንጭ: አሶሽየትድ ፕሬስ

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/26/324-8/

500 መቶ ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት የባለስልጣኑ ኦዲተሮች ጥፋተኛ ተባሉ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት 500 መቶ ሺ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በተያዙ ሁለት የገበዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኦዲተሮች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ።
ተከሳሾች አይሸሽም ገብሬ እና አክሊለብርሀን አባቡ ከባለስልጣኑ ዲኦትራኮን ወይም ጄነራል ኢትዮጵያ ኦቨርሲስ ትሬዲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቆዳና ሌጦ ግብዓት አቅራቢ ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ኦዲት አድርጉ የሚል ትእዛዝ ይሰጣቸዋል።
በታዘዙት መሰረት ኦዲት አድርገው ሳያጠናቅቁ የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ አቶ ኢብራሂም አስፋውን በሰራነው ኦዲት መሰረት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ ስለተገኘብህ 1 ሚሊዮን ብር ጉቦ ስጠን ይሏቸዋል።
ስራ አስኪያጁ  በድርድር ጉቦውን ወደ ግማሽ ሚሊዮን ዝቅ በማድረግ  ሰኔ 26 2004 ምሽት 12 ሰዓት ገደማ ሳሪስ አቦ ቀለበት መንገድ አካበበቢ ብሩን ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
ችሎቱ ከከሳሽ የኮሚሽኑ አቃቤ ህግና ከተከሳሽ የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ውሳኔ ለመስጠት ፥ ለጥቅምት 22 2006 ቀጠሮ ይዟል።

https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/26/433-5/

አንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው


የአንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው ——————————- የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት መምህር አበበ አካሉ ትናንት 14/02/06 ዓ.ም የደህንነት መስሪያ ቤት አባላት ነን ባሉ ሶስት ቅጥረኞች የግድያ ሙከራና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ለፍኖተ ነጻነት ይፋ አድርገዋል፡፡ ሰላማዊው ታጋይ እንደተናገሩት በምሳ ሰዓት ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ ህገ ወጦቹ ያካራክሯት የነበረችን ላንድክሩዘር መኪና የእግረኛ መንገድ እንድትዘጋ በማድረግ አቶ አበበን በሀይል በመኪናው በመጫን ወደማያውቁት ሰዋራ ቦታ በመውሰድ ቤቶች በሚሰሩበት አካባቢ ከመኪናዋ በማውረድ ሺሚንቶ ላይ በማስተኛት በሰላማዊ መንገድ የሚያካሂዱትን ትግል እንዲያቆሙ ይህ ካልሆነም‹‹ በሽብርተኝነት በመወንጀል መንግስትን በሀይል ለማውረድ ትሰራለህ›› በማለት እንደሚወነጅሏቸው በመንገር በቃላት ለምግለጽ በሚቸግር ሁኔታ ድብደባ እየተፈራረቁ እንዳካሄዱባቸው ተናግረዋል፡፡ መምህር አበበ ከቀኑ 6፡30 እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ግለሰቦቹ ሽጉጥ ደግነውባቸውና የማያውቁትን የአልኮል ቃና ያለው ፈሻሽ ነገር በመጋትና ከሲሚንቶ ጋር አጣብቀው በመርገጥ የግድያ ሙከራ ካደረጉበቫቸው በኋላ ከምሽት ላይ በመኪና አውጥተው እንደጣሏቸው ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ነጻነት ፓርቲው አመራሩ በህገ ወጥ መንገድ መያዛቸውንና መደብደቡን በተመለከተ ምን እያደረገ ነው በማለት የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች በመጠየቅ ከአመራሮቹ ‹‹ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንገኛለን፡፡አውሬነት የተሞላበትን አስነዋሪ ድርጊትም በቸልታ የምናልፈው አይሆንም››የሚል ምላሽ አግኝታለች፡፡ መምህር አበበ አካሉ በአሁኑ ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ይገኛሉ፡፡ ሰላማዊው ታጋይ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ናቸው፡፡
https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/26/324-8/

Friday, October 25, 2013

ዋልያዉ ጉዳት እና ጉንፋን አዳዲስ ተጫዋቾች!!!!



ለካላባሩ የመልስ ጨዋታ ዝግጅቱ ሰኞ ተጀምርዋል፤በአዲስ አበባ ስታድየም ነዉ ዝግጀቱ…ሰኞ 4ት የሳንጆርጅ ተጫዋቾ መጥተዉ ከሌሎቹ ጋሩ ቀላል ልምምድ ሰሩ፤የተቀሩት እሁድ ስለተጫወቱ  እረፍት ላይ ነበሩ፤ትላንት በተካሄደዉ ልምምድ 2ት ተጫዋቾች አልተገኙም ነበር፤አዳነ ግርማ እና አይናለም ሀይሉ ጉንፋን ስላጠቃቸዉ ነዉ ከልምምድ የቀሩት..አይናለም ጉንፋን ብቻ ሳይሆን የሆድ ህመምም አጋጥሞታል፤ሌላዉ ዛሬ በልምምድ ሜዳ ያልነበረዉ ምንያህል ተሾመ ነዉ ፤አሱም በእሁዱ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመዉ ተነግርዋል፤ነገር ግን ጉዳቱ ለክፋ ስለማይሰጥ ከነገ ወዲያ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል፤
በዋልያዉ ዙሪያ ሌላዉ አዲስ ነገር በስዩም ተስፋዬ(በ2ት ቢጫ ምክንያት አራፊ ነዉ) ቦታ ተተኪ የማግኘቱ ጉዳይ ነዉ፤እስካሁን ድረስ በቦታዉ ቢያድግልኝ ኤልያስ…አሉላ ግርማ… በተለያየ ጊዜ በቦታዉ ተጫዉተዋል፤አሉላ በናይጄሪያዉ ስብስብ ዉስጥ አለነበረም፤ከጉዳት መልስ በጥሎ ማለፍ ፍጻሜ ተጫዉትዋል፤እናም አሁን በአሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ጥሪ እንደሚደረግለት ተሰምትዋል፤ከነገ በጉዋላ ባሉት ቀናትም ይፋ ይሆናል፤ሳላሀዲን ባርጌቶ በዚህ ቦታ ለአሰልጣኝ ሰዉነት ቡድን እንደ ሌላ አማራጭ ነዉ፤
ዳያስፖራዎቹ ተጫዋቾች..አሚና አስካር እና ዋሊድ አታም የዋልያዎቹ የቤት ስራ ሁነዋል፤የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የቴከተኒክ ክፍል ልጆቹን ለማምጣት ጥረት እያደረገ ነዉ፤በተለይም ዋሊድ አታን በተመለከት ተጫዋቹን በስልክ ከማናገር እስከ ድብዳቤ ልዉዉጥ ድረስ ቴክኒክ ክፍሉ ተንቀሳቅስዋል፤አሚን አስካርንም ለመልሱ ጨዋታ ላመድረስ እንዲሁ ጥረቶች ቀጥለዋል፤ነገር ግን አሰልጣኝ ሰዉነት ተጫዋቾቹን ይፈልጉ አይፈልጉ በይፋ አልተናገሩም፤በፌዴሬሽኑ በኩል ጉዳያቸዉ እንዲታይ ከማለታቸዉ ዉጭ በቅርብ ጊዜ ፍቃድ ይሁን ተቃዉሞ አላሰሙም፤
የወዳጅነት ጨዋታን በመለከተ 2ት ቡድኖችን ለመግጠም ሙከራዎች እየተደረጉ ነዉ፤ሁለቱም የምእራብ አፍሪካ ሀገራት ናቸዉ፤በደቡብ አፍሪካ ያሸነፈችን ቡርኪና ፋሶ እና ካሜሮን ናቸዉ፤አዲሱ ፌዴሬሽን እንደቀድሞዉ አዉርቶ ጨዋታዎቹ ከሚቀሩ አረጋግጦ ማሳወቅን መርጥዋል፤
ለማንኛዉም የካላባሩ ተጠባቂ ጨዋታ 22ቀናት ብቻ ቀርተዉታል፤

 http://www.ethiotube.net

የሳውዲ የምህረት አዋጅ መገባደድና የነዋሪው ስጋት


ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ገልጿል። የሳውዲ መንግስት ሕገ ወጥ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣውን መስፈርት ለሚያሟሉ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት የሰጠው የተራዘመ የምህረት አዋጅ፤
በቀጣዩ ሳምንት ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓም ተግባራዊ ይደረጋል። በርካታ እድሉን መጠቀም የሚችሉ ሕገወጥ የነበሩ ነዋሪዎችን ጨምሮ፤ ሕጋዊ ቪዛ ይዘው ከአሰሪያቸው ውጭ በነጻነት ይሰሩ የነበሩ ጉዳያቸዉን ለማሳካት ላይ ታች ቢሉም እስካሁን ብዙዎች እንዳላጠናቀቁ ይነገራል። ከደላሎች እስከ ሃገራቸው ቆንስልና ኤምባሲ ተወካዮች፣ ከግል ቪዛ ሻጭ ሳውዲ አሰሪዎች፣ ከፊል ተወካዮች እስከ ሳውዲ መንግስት መሥሪያ ቤቶች በተወሳሰበ አሠራር ውስጥ ተዘፍቀው ጉዳያቸው ከዳር ያልደረሰዉም ቁጥር ቀላል ነው አይባልም። የተራዘመዉ የጊዜ ገደብ እየተገባደደ ባለበት በዚህ ወቅት የሳውዲ መንግስት አስፈላጊዉን አከናዉነዉ ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ ያልተቀበሉትንም ሆነ ያስጠጓቸዉን እንደሚቀጣ እያስጠነቀቀ ነዉ። ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ በዘገባዉ ገልጿል።
ነብዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሂሩት መለሠ

dw.de

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አንድን ጳጳስ ከስልጣን አነሳ


orthodox(ዘ-ሐበሻ) ነገ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎ ባደረገው ምክክር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከስልጣን አነሳ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት አባቶች  ያለ ወትሮው የኢህአዴግ መንግስት ሹማምንት በየአካባቢው በቤተክርስቲያኗ ላይ እየፈፀመ ያለውን ጥፋት በይፋ መናገርና መቃወም የጀመሩ ሲሆን፤በተለይ በዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ውሎው የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ላይ ያሉ በርካታ ችግሮችን አንስተው መወያየታቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ጋራ በተያያዘ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው በአዲሱ ፓትርያርክ ዘመን የተሾሙት መጋቢ ሀዲስ ይልማ ከድተው አሜሪካ መግባታቸው እና በከተማው አድባራትና ገዳማት ላይ የሚታየውን ስር የሰደደው ዘረኝነትና ሙስና ለማስወገድ ኃላፊነት የተሰጣቸው የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አዲስ አበባንም ደርበው እንዲሰሩ ቢሰጣቸውም ችግሮቹ ምንም ሊቀረፉ ባለመቻላቸው ከአዲስ አበባው ስልጣን እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

zehabesha

Thursday, October 24, 2013

ራስን ማጥፋት ለምን ?

ካቻምና ነሐሴ መጨረሻ ላይ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ቅጥር ግቢ ውስጥ አራት ሰዓት ተኩል ገደማ ይሆናል፡፡
በዕለቱ ምንም እንኳ ሰዓቱ በርካታ ነገሮችን ለማከናወን የወጠኑ ሠራተኞች፣ በቅጥሩ ለተለያዩ የሥራ ጉዳዮች የተገኙ ሌሎች ሰዎችም ወዲያ ወዲህ ቢሉ፤ ያለምንም ዕረፍት ሊፍቶች ቢከፈቱና ቢዘጉ እንዲሁም የእግር ዳናዎች በብዛት ቢሰሙም ሁሉም ነገር እንደተለመደው መስመር የያዘና ሰላማዊ ነበር፡፡
በቅፅበት ግን ሰዎች ይሯሯጡና ይጯጯሁ ጀመር፡፡ መናገር አቅቷቸው በድንጋጤ በቆሙበት የቀሩ፣ የሚርበተበቱና አንዲት እንኳ ቃል ማውጣት ተስኗቸው እንዲሁ እምባቸውን የሚያፈሱም ነበሩ፡፡ ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ተቀየረ፡፡ ለዚህ ምክንያት የነበረው ደግሞ በኮሚሽኑ ረዳት የሒሳብ ሠራተኛ የነበሩት ወይዘሪት አልማዝ ልዑልሰገድ ከፎቅ ላይ በመወርወር ራሳቸውን ማጥፋታቸው ነበር፡፡ የሒሳብ ሠራተኛዋ ጥሩ ክፍያ፤ ጥሩ ሊባል የሚችል ኑሮ ያላቸው ስለነበሩ ራሷቸውን የማጥፋታቸው ዜና በማኅበራዊ ድረገጾች እንዲሁም በጋዜጣ ሲታይ ብዙዎች ምን ሆነው ራሳቸውን ሊያጠፉ በቁ? ብለው እንዲጠይቁ ተገደዋል፡፡
ከደቂቃዎች በፊት በሙሉ ጤንነት የነበረ ምናልባትም ከደቂቃዎች በፊት አብረው ሻይ ቡና ያሉት ወይም ሥራን በሚመለከት ያነጋገሩት ሰው በቅፅበት ሕይወቱ አለፈ ሲባል እውነቱ ከምንም በላይ ሊቀበሉት ይከብዳል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ያ ሰው ሕይወቱን ያጠፋው በራሱ እጅ መሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ ስሜት ይረብሻል፡፡ ቀደም ሲል ፈፅሞ አንስተው ምናልባትም ስለ ሕይወት የማያውቁትን ጥያቄ በተደጋጋሚ ለራስዎ እንዲያነሱ የግድ ይላል፡፡ በዚህ ምክንያት ራስን ማጥፋት ለማኅበረሰቡ ሁሌም አስደንጋጭና በቀላሉ ለመቀበል የሚቸግር የሕይወት እውነት ነው፡፡ ከመሥሪያ ቤቱ የሥራ ባልደረቦች ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራቸው የሒሳብ ሠራተኛዋ በዕለቱ ‹‹መኖር አልፈልግም›› ሲሉ ያደመጡ ጓደኞቻቸው የሆኑትን እንዲነግሯቸው ቢጠይቋቸውም ለመግለጽ አልፈለጉም ነበር፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች በብዛት በአዕምሮ ጭንቀትና መረበሽ ውስጥ የሚያልፉ ናቸው፡፡ ጥናቶቹ እንደሚያመለክቱት ከእነዚህ ሰዎች ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆኑት በዲፕሬሽን (ድብርት) የሚጠቁ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በቅፅበታዊ ብስጭት አልያም ጭንቀት በሚፈጠር የአእምሮ መናወጥ (ሳይኮሲስ) ራስን ወደ ማጥፋት የሚያመሩ ናቸው፡፡
ፈተና ላይ ከተቀመጡ በኋላ የፈተናውን መክበድና በገመቱት አልያም በጠበቁት መጠን ጥያቄዎችን መመለስ አለመቻላቸውን በማሰብና የፈለግነውን ውጤት አጥተናል ብለው በመደምደም ራሳቸውን ያጠፉ ተማሪዎችም አሉ፡፡ እንደጭንቀታቸውና እንዳመኑት ሳይሆን በመጨረሻ ውጤታቸው ከብዙዎች በላይና ጥሩ ሊባል የሚችል ሆኖ የታየባቸው አጋጣሚዎችም በተለያየ ጊዜያት ተስተውለዋል፡፡
በድንገተኛ የአእምሮ መናወጥ ራሳቸውን ለማጥፋት የሚያስቡ ብሎም በተደጋጋሚ የሞከሩ እንደሚያጋጥሙ የኢትዮጵያ ሥነ ልቦና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሮግራም ረዳት የሆነችው ወይዘሪት ቃልኪዳን ብርሃኑ ትናገራለች፡፡ በፍቅር ግንኙነት፣ ከሥራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ራሳቸውን ለማጥፋት የሞከሩና ያልተሳካላቸው ነገር ግን በመጨረሻ የምክር አገልግሎት ሽተው ወደ ቢሯቸው ጐራ የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡
በዚህ መልኩ ካጋጠሟት ሰዎች መካከል በአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያነት የምትሠራው የ34 ዓመቷ ወጣት አንዷ ነበረች፡፡ ከዓመታት በፊት ወደ ውጭ አገር የሄደ ፍቅረኛዋ ምንም እንኳ ተለያይተው በቆዩባቸው ዓመታት ይደዋወሉ፤ በአካል ከመራራቃቸው በቀር ሁሉም ነገር እንደቀድሞ የነበረ ቢሆንም ከስድስት ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ትዳር ከመሠረተ ትንሽ መቆየቱን ይነግራታል፡፡ ይህን እውነት መቀበል እጅግ ስለከበዳት ነገሩን እንደሰማች ‹‹ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕይወቴ ትርጉም አይኖረውም›› ብላ በማሰብ ራሷን ለማጥፋት ወሰነች፡፡ ሙከራዋ ሳይሳካ በመቅረቱ በመጨረሻ የሥነ ልቦና ባለሙያ ለማየት ፈቃደኛ ሆነች፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሳይካትሪ የትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ተፈራ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ራስን የማጥፋት ሙከራ በሴቶች ቢበዛም ራሳቸውን በማጥፋት የሚሳካላቸው ግን ወንዶች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ለዚህ በምክንያትነት የሚቀመጠው ነገር ከሴቶቹ ጋር ሲነጻጸር ወንዶች ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩት አደገኛ ጉዳይ ዘዴዎችን መሆኑ ነው፡፡
እሳቸው እንደሚሉት በጥቅሉ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር ራስን ማጥፋት በአገራችን ከፍተኛ ነው ለማለት የሚያስችል መረጃ የለም፡፡ ይልቁንም መረጃዎች የሚያሳዩት ራስን የማጥፋት ነገር በተወሰነ መልኩ አነስ የሚል መሆኑን ነው፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን ከአደጉ አገሮች ጋር ሲነጻጸር በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ራስን የማጥፋት ነገር ይቀንሳል፡፡
‹‹ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ነገሮች ሰዎች ራሳቸውን እንዳያጠፉ ይገድቧቸዋል፡፡ ሃይማኖትን ብንመለከት ሁሉም ሃይማኖት ማለት ይቻላል ራስን ማጥፋትን ያወግዛል፡፡ ምንም እንኳ ሰዎች ከፍተኛ ራስን የማጥፋት ግፊት ቢኖርባቸው ከሞት በኋላ ያለን ሕይወት አስበው ሐሳባቸውን እንደሚቀይሩ በሥራ አጋጣሚዬ ብዙ ተመልክቻለሁ፡፡››
ዲፕሬሽን በተባለው ከባድ የአእምሮ ሕመም የተያዙ ሰዎች 60 በመቶ ራሳቸውን  ማጥፋት ያስባሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 15 በመቶ ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡ ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ የሆስፒታሎችና የፖሊስ ሪፖርትን መሠረት አድርጎ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው በከተማው ውስጥ በአማካይ በቀን አንድ ሰው ራሱን እንደሚያጠፋ መታወቁን ዶ/ር ሰለሞን ያስታውሳሉ፡፡
እሳቸው እንደሚሉት በቅፅበታዊ ነገር የሚወሰደው ራስን  የማጥፋት ዕርምጃ ከአጠቃላዩ አምስት በመቶ ብቻ ሲሆን፣ ብዙ የተለመደም አይደለም፡፡ ነገር ግን በሁለቱም መንገድ ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት ሲያስቡ የሚያሳዩዋቸው ያልተለመዱ ባሕርያት ሲኖሩ ይህን እንደ ምልክት መውሰድ ይቻላል፡፡ እውነታው ግን በማኅበረሰቡ ዘንድ ራስን ማጥፋት እንደነውር ስለሚታይ ችግሩም የተደበቀ ስለሆነ ራስን ስለማጥፋት አይወራም፡፡ ሰዎችም በሌሎች ላይ ስለሚመለከቷቸው የተለዩ ነገሮች ቀርበው መጠየቅ አይደፍሩም፡፡ ይህ ሰዎች ራስን ስለማጥፋት ወይም ራስን ወደ ማጥፋት ስለሚያመሩ ለውጦች እንዳይወያዩና ወደ መፍትሔ እንዳይሄዱ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡
ኤልያስ ተክሌ ከአራት ዓመታት በፊት ራሱን ስላጠፋ ጓደኛው ስንጠይቀው ጓደኛው ራሱን ያጠፋበትን ወር ዕለትና ሰዓት በትክክል ለመናገር ለቅፅበት እንኳ ማሰብ አላስፈለገውም፡፡ ነገሩ ትናንት የተፈጠረ ያህል ሁሉም ነገር በአዕምሮ በጉልህ ተሥሏል፡፡ ትውስታው ከጥልቅ ሐዘን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ስለ ሕይወት ብሩህ ምልከታ ያለው ለመኖር የሚጓጓና ነገን በተስፋ የሚናፍቅ የአብሮ አደግ ጓደኛው ራስን የማጥፋት ዜና የፈጠረበት ሐዘን ዓመታት የሚሽሩት ዓይነት አይመስልም፡፡ የጓደኛው ራሱን ማጥፋት ዛሬም ለእሱ እንቆቅልሽ ነው፡፡ እንቆቅልሹን ለመፍታት ሞክሮ ግን አያውቅም፡፡ ነገሩ ሀዘኑን ከመቀስቀስ በቀር ውጭ የሚወደው ጓደኛውን አይመልሰውምና፡፡ ኤልያስ ምንም እንኳ የጓደኛውን ሞት አምኖ ቢቀበልም ነገሩ በተለያየ መልኩ ሕይወቱን እንደቀየረው ይናገራል፡፡
ጓደኛው በብዙ መልኩ እሱ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደነበረው የሚናገረው ኤልያስ ወደኋላ መለስ ብሎ ነገሮችን በማየት ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ጓደኛው ላይ የተለያዩ የባሕሪ ለውጦች ይታዩ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ከልጅነት ጀምሮ አድገው ወደ ሥራ ዓለም ከገቡ በኋላም የጠበቀው ጓደኝነታቸው ጓደኛው ራሱን ከማጥፋቱ ከጥቂት ቀናት በፊት ሊቋረጥ የግድ ነበር፡፡ ‹‹በማይረባ ምክንያት ተጣላን›› በማለት በፀፀት ያስታውሳል ኤልያስ፡፡
‹‹መኖር ምን ያደርጋል? ሕይወት ምን ትርጉም አለው? የሚሻለው መሞት ነው የሚሉ ዓይነት ነገሮች በተደጋጋሚ ሲሰሙ ሰዎችን ቀርቦ ማነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ሞክሮ መትረፍ በራሱ አደገኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው የተረፉ ሰዎች ደግመው የመሞከር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፤›› የሚሉት ዶ/ር ሰለሞን በእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ዙሪያ ያሉ ዘመድ ጓደኞች የግለሰቦቹን የወደፊት ዕቅድ የመጠየቅና የመከታተል ሁኔታቸውን የማጥናት እንዲሁም የጤና አልያም ሌላ ችግር ካለባቸው እንዲፈታ ማድረግ እንደሚገባቸው ይናገራሉ፡፡
ራስን ስለማጥፋት ሲወራ የመጨረሻው የነፍስ ህቅታ ደቂቃዎች ምን ይመስላሉ? በብዙዎች ጭንቅላት የሚመላለስ ጥያቄ ይሆናል፡፡ ቤተሰቦቹ ላይ በነበረው ቅያሜ ከአሥር ዓመታት በፊት በአይጥ መርዝ ሕይወቱን በእጁ ለማሳለፍ የሞከረው ሽመልስ ከበደ በዕለቱ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ የተመረቀበት ነበር፡፡ ቤተሰቦቹ በተለያየ መልኩ ለሱ ዝቅተኛ አመለካከት የነበራቸው ቢሆንም የምርቃቱ ዕለት ሰፊ ድግስ ደግሰው ደስታና ፌሽታ ማድረጋቸው ለሱ ማስመሰልና ለታይታ እንደሆነ ስለተሰማው ራሱን አጥፍቶ ደስታቸውን በሀዘን በመቀየር ሊቀጣቸው አስቦ ነበር፡፡
‹‹በመጨረሻው ሰዓት አእምሮዬም አካሌም ደክሞ ነበር፡፡ ሁለቱ እህቶቼ ፊቴ ላይ ድቅን አሉብኝ፡፡ እንደገና መኖር መትረፍ ፈለግኩኝ›› ሲል አስጨናቂዎቹን ደቂቃዎች ያስታውሳል፡፡
የተለያዩ ራስን የማጥፋት ታሪኮች ሲሰሙ የአንዳንዶቹ ምክንያት ሕይወትን ለማጥፋት በቂ አይደለም ሊያስብል ቢችልም በቂ ነው አይደለም ብሎ ለመደምደም ምናልባትም በጉዳዩ ባለቤቶች ቦታ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ የወደዳት ልጅ የፍቅር ጥያቄውን ያልተቀበለችው አንድ የአሥረኛ ክፍል ተማሪ ራሱን ሲያጠፋ ጥሎ ያለፈው መልዕክት ‹‹የምፈልገውን ነገር እያጣሁኝ ለምን እኖራለሁ?›› የሚል ነበር፡፡
በቅፅበታዊ ንዴት ወይም ጭንቀት ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች ነገሮችን የሚያስተናግዱበት ሥነ ልቦናዊ አቅም ያልዳበረ ነው፡፡ ራስን የማጥፋት ዕርምጃውን ለመውሰድም በውስጣቸው ብዙ ትግል ይፈጠራል፡፡ ሙከራቸውም አብዛኛውን ጊዜ የተሳካ አይሆንም፡፡
ዶ/ር ሰለሞን የሚመለከቷቸው ሕመምተኞች ከሞላ ጎደል ሁሉም በከፍተኛ ዲፕሬሽን የሚሰቃዩ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም ዓይነት የኑሮ ችግር የሌለባቸው ምናልባትም ሁሉ የተሟላላቸው ነገር ግን በከባድ የአዕምሮ ሕመም የሚሰቃዩ ናቸው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች እያንዳንዱ ቀን ሊሸከሙት የማከብድ፣ የእያንዳንዱ ቀን ብርሃን ሊቋቋሙት የማይቻል ይሆናል፡፡ በሰላም አሳድረኝ በማለት ፈንታ ወደ አልጋቸው ሲሄዱ ዕለቱ የመጨረሻ የሕይወት ቀናቸው እንዲሆን ፈጣሪያቸውን የሚለምኑና ነግቶ ራሳቸውን በሕይወት ሲያገኙ እጅግ የሚበሳጩ ሰዎች በተደጋጋሚ አጋጥመዋቸዋል፡፡
‹‹የተማረ፣ የተደራጀ ኑሮ ያለው በሁሉም መስፈርት ቢመዘን ጥሩ የሚባለ ኑሮ ያለው አንድ ሕመምተኛ ነበረኝ፡፡ እያንዳንዱን ቀን የሚያሳልፈው ያለምንም ስቃይ እንዴት በቀላሉ ራሱን ማጥፋት እንደሚችል ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ ነበር፡፡›› በማለት አጋጣሚውን ያስታወሱት ዶ/ር ሰለሞን እንደዚህ ያሉት ሰዎች ራስን የማጥፋት ነገር በውጫዊ ሁኔታዎች ሳይሆን በውስጣዊ የአዕምሮ ሕመም የተጫነባቸው እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡
ዶ/ር አብድልረሺድ አብዱላሒ በክሪ ራስን ማጥፋትን በሚመለከት የፖሊስና የሆስፒታሎችን ሪፖርት መሠረት በማድረግ አዲስ አበባ ላይ አትኩረው የሠሩት ጥናት እንደሚያሳየው በ15 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ የሴት ራስን የማጥፋት ጥቅል ሬት 2.45 ሲሆን፣ የወንዶች ደግሞ 12.7 ነው፡፡ በብዛት የሚታየው ራስን የማጥፋት ዘዴ መታነቅ ሲሆን፣ ይህ 70.2 በመቶ ይሆናል፡፡
ሰዎች አፍረው እውነቱን ለመናገር ባይደፍሩም በርካታ ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው በተለያየ አጋጣሚ ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረዋል ወይም አስበዋል፡፡ በ1974 ዓ.ም. ራስን የማጥፋት እንዲሁም ምክንያቱ ያልታወቀ ሞት 88 የነበረ ሲሆን፣ 1988 ይህ ቁጥር ወደ 269 አድጓል፡፡ ከዚህ ውስጥ የወንዶችና የሴቶች ምጣኔ 5.19፡1 ነው፡፡ ጥናቱ በተደረገባቸው 15 ዓመታት የተወሰዱ ራስን የማጥፋት ዕርምጃዎች ራስን መስቀል (1502)፣ ውኃ ውስጥ መግባት (328)፣ መርዝ (161) እና ያልታወቁ መንገዶች (150) ነበሩ፡፡
በወቅቱ የተደረጉ ራስን የማጥፋት ሙከራዎች በመቶ ሺሕኛ ሲሰሉ 1974 ዓ.ም. 1092 ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በ1988 ወደ 3675 አድጓል፡፡
ጥናቱ እንደሚያሳየው ራስን የማጥፋት ሙከራዎች አብዛኛውን ጊዜ ለሆስፒታል ሪፖርት ስለማይደረጉ ከተደረጉም እንደ ድንገተኛ አደጋ ተደርገው ስለሚቀርቡ ቁጥሩ ትክክለኛውን ነገር ላያሳይ ይችላል፡፡ ጥናቱ በእሳት ቃጠሎ፣ በፈንጂ፣ በስለት፣ ከከፍታ በመዝለል የመሳሰሉ ራስን ማጥፋቶችን አይጨምርም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ አጋጣሚዎች እንደ ድንገተኛ አደጋ ሊታዩ ይችላሉና፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩት ወጣቶች በመሆናቸው ራስን ማጥፋትን መከላከል ላይ ቢሠራ የዕርምጃው አንድምታ ትልቅ ነው፡፡ ምንም እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለውጦች ቢኖሩም ሰዎች የአዕምሮ ሕመምን እንደ ማንኛውም አካላዊ ሕመም አይተው ወደ ባለሙያ ለመሄድ ያላቸው ተነሳሽነት ዛሬም ዝቅተኛ ነው፡፡ ከሚመለከቷቸው ሕመምተኞች አብዛኞቹ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ መፍትሔዎችን ሞክረው በመጨረሻ ወደ ሕክምና ለመሄድ የወሰኑ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት በአማኑኤል ሆስፒታል በአንድ ሺሕ ሕመምተኞች ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው ሌሎች አማራጮችን ሳያዩ ሕክምናን እንደ ቀዳሚ መፍትሔ ተመልክተው ወደ አዕምሮ ሐኪም የሄዱ ታካሚዎች ከግማሽ በመቶ በታች ናቸው፡፡
ዓለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ራስን ማጥፋት ባደጉት አገሮች ሁለት ዓይነት ሥርጭት (Bi-polar Distribution) አለው፡፡ ይህ ሥርጭት ራስን ማጥፋት በብዛት የሚታየው በወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ እንዲሁም ዕድሜያቸው በገፋ ሰዎች ነው፡፡ ወጣትነት የሽግግር ጊዜ እንደመሆኑ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት የመፈተኛ ጊዜም ነው፡፡ በሌላ በኩል እርጅና ብቸኝነት የሚጫንበት ድካም የሚመጣበት ነው፡፡ ይህ የሚያሳድረው ጭንቀት ራስን ወደ ማጥፋት ሊያመራ ይችላል፡፡ በእኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ ግን ማኅበራዊ ትስስር ጠንካራ በመሆኑ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ብቸኛ ስለማይሆኑ፣ በዕድሜያቸው ተከብረው ለሽምግልና የሚፈለጉ በመሆኑ፣ በብዛት ወደ ቤተ ክርስቲያን ፊታቸውን የሚመልሱበት ጊዜ በመሆኑ ራሳቸውን የሚያጠፉበት ሁኔታ አለመኖሩን ዶ/ር ሰለሞን ይገምታሉ፡፡ ይልቁንም የሚያውቋቸው ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች በወጣት አልያም በአዋቂነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሥርጭቱ ወጣቶችን በሚመለከት በአገራችንም የሚታይ እውነት ነው፡፡
የኢኮኖሚ ሽግግር፣ የውጭ ባሕል ተፅዕኖና የአኗኗር ዘዬ ለውጥ በአገራችን እውነታ በምን ያህል ደረጃ ራስን ለማጥፋት አስተዋጽኦ የደርጋሉ? የሚል ጥያቄ ለዶ/ር ሰለሞን አንስተን ነበር፡፡
እንደ እሳቸው ገለጻ ማኅበራዊ ሽግግር በራሱ ለአዕምሮ ጤና አደጋ ነው፡፡ በአገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባሕላዊ ሽግግሮች እየታዩ ነው፡፡ ስለዚህ በተለይም ወጣቱ እነዚህ ሽግግሮች በሚፈጥሯቸው ግፊቶች የተወጠረ ነው፡፡ ግፊቶቹ የተወሰኑት ጠቃሚ ሌሎቹ ደግሞ ጐጂዎች ናቸው፡፡ ግላዊነት፣ ደስታን በማንኛውም መንገድ መሻት ራስን ወደማጥፋት ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ በማንኛውም መንገድ ደስታን መሻት የተለያዩ አነቃቂ እፆችን ወደ መጠቀም ያመራል፡፡ እነዚህ አነቃቂ እፆች ደግሞ ለዲፕሬሽን ያጋልጣሉ፡፡
ሽግግሮቹ ኑሮ ላይ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ ሁሉም ሰው ከእነዚህ ሽግግሮች ጋር ለመራመድ ይሮጣል፡፡ በዚህ ሩጫ ውስጥ የሚሳካላቸው አሉ፡፡ የማይሳካላቸው ደግሞ ከፍተኛ የኑሮ ጫና ሊያድርባቸውና ለዲፕሬሽን ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ በአንድ ወቅት በከተማችን በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ያጠፉ ታዋቂ ባለሀብቶች ታሪክ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ሽግግሮች የሚፈጥሩት ጫና እንዴት ራስን ለማጥፋት ምክንያት እንደሚሆን ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያው ያምናሉ፡፡
‹‹ሰው ራሱን ወይም ሌላ ነገሩን ሲያመው ወደ ሐኪም እንደሚሄድ ሁሉ ራሱን የማጥፋት ፍላጎት በውስጡ ሲፈጠር ለምን መኖር ያስጠላኛል? ለምን ራስህን አጥፋ አጥፋ ይለኛል? ብሎ በመጠየቅ ወደ አዕምሮ ሐኪም በመሄድ የነገሩን መፍትሔ ለማግኘት መሻት አለበት፡፡ ምክንያቱም ችግሩ በምክር በሕክምና የሚፈታ ነውና››
ዶ/ር ሰለሞን ራስን አጥፋ የሚል ነገር ወደ አዕምሮ ስለመጣ ወይም ችግሮችን (የኑሮ) በአቋራጭ ለማምለጥ ራስን የማጥፋት ዕርምጃ ውጤቱ አስከፊ ይሆናል ይላሉ፡፡ ሕይወቱን ለሚያጣው ሰው ጉዳት ለቀሪ ቤተሰብ ዘመድም የልብ ስብራት ያስከትላል፡፡ ለሚቀርቡትና የመፍትሔ አቅጣጫ ሊያሳየኝ ይችላል ለሚሉት ቤተሰብ ጓደኛ ችግርን መንገርም መሸነፍ ደካማነትም እንዳልሆነ ማመን ያስፈልጋል፡፡
በአማኑኤል ሆስፒታል በጥናትና ሥልጠና ክፍል የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዘገየ ዮሐንስ እንዳሉት ራስን ማጥፋት የአዕምሮ ሕመም አንዱ ምልክት ነው፡፡ ምንም እንኳ በከፍተኛ ሁኔታ ራስን ለማጥፋት ምክንያት የሚሆነው ዲፕሬሽን ቢሆንም ስኪዞፍሬኒያ፣ አደጋን (አጋጣሚን) ተከትሎ የሚደርስ የአዕምሮ ሕመም፣ ጭንቀትና ሌሎችም የአዕምሮ ችግሮች በተለያየ ደረጃ ራስን ለማጥፋት ምክንያት ይሆናሉ፡፡
አቶ ዘገየ እንደሚሉት ራስን ማጥፋት ምክንያቱ ይሄ ነው ያ ለማለት በሚያስችል መልኩ የተጠና ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቶቹ ባዮሎጂካል፣ ሥነልቦናዊ አልያም ማኅራዊ ነገሮች ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ መፍትሔውም የተለያዩ ነገሮችን አቀናጅቶ የያዘ ነው፡፡ በፈተና ወቅት የሚፈጠር ጭንቀት፣ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነገርና ጦርነት የተወሰኑ ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
ethiopian reporter

‘‘መላኩ ፈንታ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሶስት ልጆች እናትን ከትዳሯ አፋተው አግብተዋል’’ – ዐቃቤ ሕግ


በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር

የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል።
ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክሱ ሲነበብ፤ 1ኛው ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሷቸዋል።
Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgis
ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን በክስ መዝገቡ ያትታል።
በዚህም መሠረት ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል የሙስና ክስ መስርቷል።
ዐቃቤ ህግ በዚህ ክስ ዝርዝር ውስጥ በተጨማሪነትም ተከሳሽ በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ ተዝናንታለች ሲል፤ የተፈፀመው ወንጀል መንግስትና ህዝብ የጣለበትን አደራ ያለአግባብ የመጠቀም ሙስና ሰርቷል ይላል። (በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉትን 24 ተከሳሾች የክስ ሙሉውን ጭብጥ እነሆ)
ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አዲስ አበባ
የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ/መ/ቁ.
የዐ/ህ/መ/ቁ.
የከ/ፍ/ቤ/ወ/መ/ቁ/ 141352
ከሣሽ ………….. የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮማሽን ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች ……… 1ኛ/ አቶ መላኩ ፈንታ ቻይ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋ/ዳይሬክተር
2ኛ. አቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር
3ኛ. አቶ በላቸው በየነ ገ/ጊዮርጊስ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
4ኛ. አቶ ማርክነህ አለማየሁ ወዴቦ
ሥራ፡- ም/ዋና ዐ/ሕግ
5ኛ. አቶ እሸቱ ግረፍ አስታክል
ሥራ፡- ገ/ጉ/ባለሥልጣን አ.አ ቃሊቲ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊ
6ኛ. አቶ አስፋው ስዩም ተፈራ
ሥራ፡- ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ
7ኛ. አቶ ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ሥራ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዳማ ቅ/ፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ
8ኛ. አቶ አስመላሽ ወ/ማርያም ገብሬ
ሥራ- የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ የነበረ
9ኛ. አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ደበበ
ሥራ፡- ነጋዴ
10ኛ. አቶ ከተማ ከበደ አስገልጥ
ሥራ፡- የግል ባለሀብት
11ኛ. አቶ ስማቸው ከበደ ካሳ
ሥራ፡- ነጋዴ
12ኛ. ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ወርዶፋ
ሥራ፡- ሐኪም
13ኛ. ኮ/ል ኃይማኖት ተስፋዬ ገ/ስላሴ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን ም/ስራ አስኪያጅ
14ኛ. አቶ ዳንኤል ገ/ኪዳን (ያልተያዘ)
ሥራ፡- የግብር አውሳሰንና ምርመራ ኦዲተር
15ኛ. አቶ አውግቸው ክብረት
ሥራ፡- ዐቃቤ ሕግ
16ኛ. አቶ ጌቱ ገለቴ (ያልተያዘ)
ሥራ፡- ነጋዴ
17ኛ. አቶ ገ/ስላሴ ገብረ ኃ/ማርያም
ሥራ፡- ነጋዴ
18ኛ. ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ሥራ፡- ጄ.ኤች.ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
19ኛ. ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
20ኛ. ነፃ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
21ኛ. ጌታስ ኃ/የተ/የግ ማኅበር
22ኛ. ኮሜት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
23ኛ. አቶ ፍፁም ገብረመድህን አብርሃ
ሥራ፡- ነጋዴ
24ኛ. አቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ
1ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ እና 10ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 10ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
- 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች በ2001 ዓ.ም በተካሄደው አራጣ አበዳሪዎችን ለሕግ የማቅረብ ተግባር በተጀመረበት ወቅት ለተከሳሹ በጥቆማ መልክ ከቀረቡት ዘጠኝ አራጣ አበዳሪዎች ስም ዝርዝር መካከል 10ኛ ተከሣሽ አራጣ አበዳሪ መሆኑን የሚያስረዱ ማስረጃዎች ቀርበውለት እያለ የተከሳሹ ጉዳይ በምርመራ ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርብ ማድረግ ሲገባው ከዚህ በተቃራኒው ከተከሣሹ ጋር በፈጠሩት ሥውር የጥቅም ግንኙነት ሌሎች አራጣ አበዳሪዎች ምርመራ ተጣርቶባቸው ለሕግ ሲቀርቡ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት 10ኛ ተከሳሽ ላይ ምርመራ እንዳይጣራና ሕግ ፊት ቀርቦ እንዳይጠየቅ በማድረጋቸው፣
- 10ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ አራጣ አበዳሪነቱን የሚያስረዱ ማስረጃዎች ቀርቦበት እያለና ሌሎች አራጣ አበዳሪዎች ሕግ ፊት ቀርበው ሲከሰሱ ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ጋር በስውር በፈጠረው ሚስጥራዊ የጥቅም ግንኙት በአራጣ አበዳሪነቱ ምርመራ እንዳይጣራበትና ሕግ ፊት ቀርቦ እንዳይጠየቅ የ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕወቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳኃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
2ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጰያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 11ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
- 1ኛ ተከሣሽ በ2003 ዓ.ም ለሆቴል አገለግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ያስገቡ ሆቴሎች ከቀረጥ ነፃ ያስገቡትን ዕቃ ከታለመለት ዓላማ ውጭ እየተገለገሉበት ስለመሆኑ መረጃ ደርሶት ጉዳዩ በባለሥልጣኑ የኢንተለጀንስ ክፍል ጥናት እንዲደረግ ተወስኖ ጥናትና የኦዲት ክትትል ከተደረገ በኋላ ጥናት ከተደረገባቸው ሆቴሎች መካከል አንዱ ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር (ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ሲሆን በተካሄደው ጥናትና የኦዲት ክትትል መሠረት ወንጀል መፈፀሙን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ቀርቦ እያለና ሌሎች ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሆቴሎች ምርመራ እንዲጣራባቸው ሲደረግ የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በ26/11/2002 እና በ19/16/03 ዓ.ም በተደረገው ቆጠራ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ከ11ኛ ተከሣሽ ጋር በስውር በመመሣጠር የተፈፀመው ሕገወጥ ድርጊት ምርመራው እንዳይጀመርና ተከሳሹ ለሕግ እንዳይቀርብ በማድረጉ፣
- 2ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ከላይ በተ.ቁ. 1 በተጠቀሰው ጊዜና አኳሃን የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በተካሄደው ቆጠራ ተረጋግጦና ሌሎች ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሆቴሎች ምርመራ እንዲጣራባቸው ሲያደርግ ከ11ኛ ተከሳሽ ጋር በስውር በመመሳጠር ከላይ በተጠቀሰው ሆቴል ላይ ምርመራው እንዳይጀመርና ለሕግ እንዳይቀርብ በማድረጉ፣
- 3ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኃን የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ ማዋል አለማዋሉን ለማረጋገጥ ቡድን አቋቁሞ ወደ ሆቴሉ በመላክ በተደረገው ቆጠራ ብር 9‚981‚651.83 (ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ከ83/100) ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በቡድኑ ተረጋግጦ እያለ ተከሣሹ አቤቱታ እንዲያቀርብና ድጋሚ ቆጠራ እንዲደረግ ከማድረጉም በላይ በድጋሚ ቆጠራውም ብር 8‚716‚012.84 (ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ስድስት ሺህ አስራ ሁለት ብር ከ84 ሳንቲም) እንዲከፍል በመወሰን ድርጅቱ ምርመራ እንዳይጣራበትና በወንጀል እንዳይከሰስ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱ፣
- 11ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኃን ለድርጅቱ መገልገያ የሚሆኑ የሆቴል ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ተፈቅዶለት አስገብቶ ለተፈቀደለት ዓላማ ማዋል ሲገባው ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ መጠቀሙን በገ/ጉ/ባለሥልጣን ባለሙያዎች ተረጋግጦ እያለ በፈፀመው ድርጊት በወንጀል መጠየቅ ሲገባው ከ1ኛ-3ኛ ከተጠቀሱት ተከሣሾች ጋር በጥቅም በመመሣጠር ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ በወንጀል እንዳይጠየቅ በማድረግ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በሙሉ ፈቃደቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተከፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃለፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
3ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ፣ እና 12ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 12ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
- 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች 12ኛ ተከሳሽ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ከስዊድን ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመባቸውንና ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን 32 ዓየነት የተለያዩ ብዛት ያላቸው የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በአራት ሻንጣ ሲያስገባ ተይዞ 5% ቀረጥና ታክስ ከፍሎ ወደ መጣበት ሀገር እንዲመልስ ተወስኖ ሕዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም ታግ ተለጥፎበት ቤልት ላይ ከገባ በኋላ ከሀገር እንዲወጣ የተባለውን ዕቃ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደብቆ መልሶ ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ ሲል ተይዞ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 9/1/ የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀመው የኮንትሮባንድ ወንጀል በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሶ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ካጠናቀቀ በኋላ ለፍርድ ተቀጥሮ ባለበት ሁኔታ ከተከሳሹ ጋር በፈጠሩት ሕግ ወጥ የጥቅም ግንኙነት እንዳይቀጣ በማሰብ ለፍርድ የተቀጠረውን ክስ ያለ ሕጋዊ ምክንያት እንዲነሳ በማድረጋቸው፣
- 12ኛ ተከሣሽም በፈፀመው ወንጀል ተከሶ የነበረ ቢሆንም ከ1ኛ እና የ2ኛ ተከሳሾች ጋር በፈጠረው የጥቅም ግንኙነት የተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ ክሱን በማስነሳት ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሣሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳኃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
4ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ፣ 16ኛ፣ 17ኛ እና 24ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ፣ 2ኛ፣ 8ኛ እና 24ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ፤ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ እና 24ኛ ተከሳሽ ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ ሲሆኑ፣ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾችም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
ከ1999 ዓ.ም እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የሲሚንቶ እጥረትና ዋጋውን ለማረጋጋት ከውጪ አገር ያለ ውጪ ምንዛሪ ክፍያ ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለሀገራዊ የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ ለማዋል ታሰቦ የገባው ሲሚንቶ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለ3ኛ ወገን በመተላለፉ ቀኑና ወሩ ለጊዜው ባልታወቀበት 2002 ዓ.ም ለ2ኛ ተከሳሽ እና እሱ ለሚመራው የሕግ ማስከበር ዘርፍ ጥቆማ ተደርጎ የብር 21‚602‚608.64 /ሃያ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስምንት ብር ከ64/100/ ቀረጥና ታክስ ባለመከፈሉ በመንግስት ላይ ጉዳት መድረሱ በመረጋገጡ ውሉን የተዋዋለው አቅራቢው ድርጅት፣ ትራንዚተሮች፣ ሲሚንቶውን በትራንስፖርት አስገብተው ለ3ኛ ወገን አሳልፈው የሰጡ አጓጓዥ ድርጅቶች እና ስራ አስኪያጆቻቸው ወይም ባለንብረቶቻቸው እንዲሁም ቁጥጥርና ክትትል ያላደረጉት የጉምሩክ ሰራተኞች ጭምር ተጠያቂ መሆናቸው በኣዲት ተረጋግጦ ቀርቦ እያለ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ምርመራ በማጣራት አጥፊዎችን ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ሲገባቸው ከዚህ በተቃራኒው በመስራት ሕገወጥ ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ፣
- 1ኛ ተከሳሽ የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ እንደመሆኑ የመ/ቤቱ ሰራተኛ የሆነው 8ኛ ተከሳሽ በደንብ ቁጥር 155/2000 መሰረት በፈፀመው ድርጊት በወንጀል እና በዲሲፒሊን እንዲጠየቅ ማስደረግ ሲገባው በፈፀመው ድርጊት እንዳይጠየቅ ከማድረጉም በተጨማሪ በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሲቀርብበትም ተከሳሹን ለሕግ ማቅረብ ሲገባው ስራውን እንዲለቅ ማመልከቻ እንዱያቀርብ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱና ሊጠየቁ በሚገባቸውም ሲሚንቶውን ባስገቡትና ባጓጓዙት በሁሉም የትራንስፖርት ድርጅቶች ላይ ክስ እንዲቀርብ ባለማስደረጉ፤
- 2ኛው ተከሳሽ በበላይነት በሚመራው የስራ ዘርፍ ምርመራው ሲጣራና ክሱ ሲቀርብ የባለስልጣኑ መ/ቤት ሰራተኛ የሆነው 8ኛ ተከሳሽ ቃሉን እንዳይሰጥ በማስደረግ፣ ደመወዝ እየተከፈለው ስራ ላይ ያለ ሰራተኛ መሆኑን እያወቀ ያለአግባብ በጋዜጣ ሲጠራም በዝምታ በማለፍ በመጨረሻም ከ1ኛው ተከሳሽ ጋር ተመካክሮ ተከሳሹ ስራውን እንዲለቅ በማስደረጉ እንዲሁም ሊከሰሱ ከሚገባቸው የትራንስፖርት ድርጅቶችና ባለንብረቶች ጋር ባለው ስውር የጥቅም ግንኙነት ምክንያት የራሱና የሌሎችን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ጉዳዩን እንዲያጣራ ምንም ኃለፊነት ካልተሰጠው የደህንነት መ/ቤት ከፍተኛ አመራር ከሆነው 24ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን እያስቀረበ ከመረመረ በኋላ ወንጀል የተፈፀመበት ሲሚንቶ የሌላ ሰው ነው ብላችሁ መስክሩ በማለት የጉዳዩን አቅጣጫ እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ከመገፋፋቱም በላይ ኤ ኤንድ ጂ ድርጅት፣ ኃይሌ አሰፋ እና ሸሚዛል በተባሉት 3 ድርጅቶች ላይ ብቻ ምርመራው ተጣርቶ ክሱ እንዲቀርብ ሲያስደርግ ከእሱ ከ24ኛ ተከሳሽ ጋር የጥቅም ግንኙነት ባላቸው 1ኛ. ነፃ ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 9ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ. ጌታስ የተባለው ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 16ኛ ተከሳሽ እና 3ኛ. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 17ኛ ተከሳሽ ላይ ተነጥሎ ምርመራ እንዳየጣራባቸው በማስደረጉ፤
- 24ኛ ተከሳሽም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መ/ቤት ውስጥ ከፍተኛ መዋቅር ላይ ተመድቦ ሲሰራ ይህን ስልጣንና ኃላፊነቱን አለአግባብ መከታ በማድረግ ከቀረጥ ነፃ የገበያ ሲሚንቶ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ለገቢዎችና ጉምረክ ባለስልጣን የቀረበውን ጥቆማና ምርመራ እንዲከታተል ከመ/ቤቱ ባልተወከለበት ሁኔታ የራሱና የሌሎችን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ በተለያዩ ቅናት 2ኛ ተከሣሽቢሮ ድረስ በመሄድ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን እያስቀረበ ከመረመረ በኋላ ወንጀል የተፈፀመበት ሲሚንቶ የሌላ ሰው ነው ብላችሁ መስክሩ በማለት የጉዳዩን አቅጣጫ እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ሙከራ ከማድረጉም በላይ ኤ ኤንድ ጂ ድርጅት፣ ኃይሌ አሰፋ እና ሸሚዛል በተባሉት 3 ድርጅቶች ላይ ብቻ ምርመራው ተጣርቶ ክሱ እንዲቀርብ ሲያስደርግ ከእሱና ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር የጥቅም ግንኙነት ባላቸው 1ኛ. ነፃ ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 9ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ. ጌታስ የተባለው ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 1ኛ ተከሳሽ እና 3ኛ. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 17ኛ ተከሳሽ ላይ ተነጥሎ ምርመራ እንዳይጣራባቸው በማስደረጉ፤
- 8ኛ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ተከሶ ፍ/ቤት እንዲቀርብ የታዘዘ ቢሆንም ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር ባለው የጥቅም ትስስር እና የነሱን ሽፋን ተጠቅሞ ፍ/ቤት ቀርቦ እንዳይጠየቅ በማስደረጉ፣
- 9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾችም ከቀረጥ ነፃ የገባ ሲሚንቶ አጓጉዘው ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለ3ኛ ወገን ለመሸጣቸው ተረጋግጦ እያለ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ባላቸው የጥቅም ትስስር ምክንያት በምርመራው እንደይካተቱ የ2ኛ ተከሳሽን ሽፋን አግኝተው በሕግ እንዳይጠየቁ በማስደረጋቸው፣ ሁሉም ተከሳሾች ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
5ኛ ክስ
በ1ኛ፣ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
- 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ኢኖቫ ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እ.ኤ.አ በ2009 ለመንግስት መከፈል የነበረበትን ገቢ ግብር ብር 2‚088‚328.72 (ሁለት ሚሊየን ሰማንያ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም) ግብርን አሳውቆ ባለመክፈሉ እና ዓመታዊ ትርፉ 11‚448‚939.30 (አሥራ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ብር ከሰላሳ ሳንቲም) ሆኖ እያለ በበጀት ዓመቱ ያሳወቀው ግብር ብር 9‚569‚671.05 (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሣ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር ከዜሮ አምስት ሣንቲም) ነው ብሎ አሳሳች ማስረጃ በማቅረቡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96፣ 102፣ 97/1/ እና 3(ለ) የተመለከተውን ተላልፎ ሕግን በመጣስ ግብር አለመክፈልና አሳሳች መረጃ ማቅረብ ተደራራቢ ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ በድርጅቱና በድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ላይ በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ እያለ ድርጅቱና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅን ከወንጀል ተጠያቂነት ለማዳን በማሰብ 2ኛ ተከሳሽ ክሱ እንዲነሳ ለ1ኛ ተከሳሽ በ7/2/2005 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ 1ኛ ተከሳሽ አፅድቆ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት ክሱን እንዲነሳ በማድረጋቸው፣ ሁለቱም ተከሣሶች በሙሉ ፈቃደቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግሰትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
6ኛ ክስ
በ2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆን፤ ስልጣንና ኃለፊነቱን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
- 2ኛ ተከሣሽ በ26/07/2001 ዓ.ም ጐላጐል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተባለ ድርጅት ያለቫት ደረሰኝ ግብይት እንደሚፈፅም ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጥቆማ ቀርቦ እውነተኛነቱን ለማረጋገጥ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ተልከው እንደጥቆማው አቀራረብ እንደሚፈፅም በወቅቱ በተላኩት ሠራተኞች ከተረጋገጠና ተጠርጣሪዎችም ከተለዩና ምርመራ መዝገቡ ተደራጅቶ እንደሚያስከስስ ከተረጋገጠ በኋላ ተከሣሹ የባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የድርጅቱ ባለቤት አቤቱታ ስላቀረበ ጉዳዩ በድጋሚ መታየት አለበት በሚል ሽፋን ምርመራው እንደገና እንዲጣራ በማድረግ ቀደም ሲል በጉዳዩ ዙርያ ከተሰጠው የምስክርነት ቃል በተለየ ጉዳዩን ሊያዳክም የሚችል አዲስ ተጨማሪ ቃል እንዲቀርብ በማድረግ መዝገቡ ውጤት እንዳይኖረው ካመቻቸ በኋላ ምርመራ መዝገቡ እንዲዘጋ በማስደረጉ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው የመንግስት ሥራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
7ኛ ክስ
በ2ኛ፣ እና 7ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፤
- ገላን ታነሪ ኃ/የተ/የግ ማኅበር የተባለው ድርጅት በዲክላራሲዮን ቁጥር E-3248/1 ወደ ውጭ ለመላክ ዲክሌር ያደረገው የቆዳ ብዛት 33‚600.00 (ሰላሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ) ሆኖ በአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ11/03/04 ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ ብዛቱ 42‚360 (አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ) ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት በልዩነት ለተገኘውና ግምቱ ብር 423‚189.94 (አራት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ከ94/100) ለሆነው 8‚760 (ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ) ቀዳ በድርጅቱ እና በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ኑር ሐሰን ላይ የወንጀል ምርመራ ተጣርቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ በቁጥር 8-54593/04 በ26/08/2004 የተዘጋጀ ክስ አቅርቦባቸው እያለ፤
7ኛ ተከሳሽ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በነበረው ኃላፊነት ባለሀብቱ ወደ ውጪ ለመላክ ባቀረበው ቆዳ ላይ ፍተሻ በሚደረግበት ወቅት ቆዳ በትርፍነት የተገኘበትና ምርመራም የተጣራበት መሆኑን እያወቀ ባለሀብቱንና ድርጅቱን ከተጠያቂነት ለማዳን አስቀድሞ በቁ.8.0/0/1048 በ12/06/04 ለድርጅቱ በፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩን ለዐቃቤ ሕግ እንደማይልክ ከመግለፁም በተጨማሪ በባለሀብቱ ላይ የቀረበው ክስ እንዲነሳ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ በ15/09/04 በተፃፈ ቃለ ጉባኤ ለ2ኛ ተከሳሽ በማቅረቡ፣ 2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ባለሀብቱ የማታለል ድርጊት በመፈፀም ቆዳ በትርፍነት ለመላክ ሲሞክር መያዙን እያወቀ በባለሀብቱ ላይ የተመሰረተው ክስ የሚነሳበት ሕጋዊ ምክንያት በሌለበት ሁኔታ ከባለሀብቱ ጋር በጥቅም በመመሳጠር በባለሀብቱ ላይ የቀረበው ክስ እንዲቋረጥ በ24/09/04 ትዕዛዝ በመስጠት ክሱ እንዲነሳ በማድረጉ፣ ሁለቱም ተከሳሾች ባለሀብቱ በሕግ እንዳይጠየቅና በትርፍነት የተገኘው ቆዳ ላይም እርምጃ እንዳይወሰድ በማድረጋቸው፣ በተሰጣቸው የመንግሠት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
8ኛ ክስ
በ2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆን፤ ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
- 2ኛ ተከሣሽ አቢ ብርሃኑ የተባለ ግለሰብ ተገቢው ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸውን የሰሌዳ ቁ.ኮድ 3-48863 አ.አ. እና ተላላፊ ሰሌዳ ቁ.545 አ.አ. የሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ይዞ በ30/01/2001 ዓ.ም በመገኘቱ ምክንያት ከሌላ ግብረአበሩ ጋር ምርመራ ተጣርቶበት መዝገቡ ለሚመለከተው ዐቃቤ ሕግ ከተላለፈ በኋላ ተከሳሹ ሥልጣኑን በመጠቀም በመዝገቡ ውስጥ 1ኛ ተጠርጣሪ ከሆነው አቢ ብርሃኑ ከተባለው ተጠርጣሪ አባት አቶ ብርሃኑ ብሩ ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት እንዳይሄድና መኪናውም እንዲለቀቅ ለማድረግ ከተያዙት ሁለት መኪኖች ውስጥ ኮድ 3-48863 አ.አ የሆነው መኪና በአዋጅ ቁ. 60/89 አንቀፅ 74 መሠረት መወረስ እየተገባው ቀረጥና ታክሱ ተከፍሎ እንዲለቀቅ በማድረግ በዚህም መነሻነት የወንጀል መዝገቡ እንዲዘጋ በማድረጉና ለዚህም ውለታው በአሁኑ አጠራር ለገጣፎ ለገዳዲ በቀድሞ ስሙ ወልገወ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሊቀመንበር በነበረው አቶ ብርሃኑ ብሩ አማካኝነት በአሁኑ ሰዓት ሊገኝ ያልቻለ ሕገ ወጥ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ በመስጠትና በዚህም መታወቂያ መነሻነት በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ 500 ካ.ሜ ቦታ በሕገወጥ መንገድ በመውሰዱ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀመው የመንግስት ሥራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
9ኛ ክስ
በ2ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሶች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ፣ ምክትል ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ በዐቃቤ ቃሊቲ ቅ/ፅ/ቤት የሕግ ማስከበር ኃላፊ እና የድሬ ዳዋ ቅ/ፅ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
6ኛ ተከሳሽ በ8/8/2002 ዓ.ም በባለሥልጣኑ አዋሽ መቅረጫ ጣቢያ ማንነቷ ለጊዜው ካልታወቀች ግለሰብ ላይ በፍተሻ ከተያዙ ኮንትሮባንድ ካሜራዎች ውስጥ ሦሰት ሶኒ ጂጅታል ካሜራዎችን ወስዶ ለግል ጥቅሙ ማዋሉ ታውቆ ምርመራ መጣራት ሲጀመርበት፡-
- 5ኛ ተከሣሽ የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ የሆኑትን አቶ ምንይችል ተኮላ ጋር ስልክ ደውሎ “6ኛ ተከሳሽ ለምን ታሰረ? እንዲፈታ!” ብሎ በቃል ትዕዛዝ ከማስተላለፉም በላይ በአካል ከሥፍራው ድረስ በመሄድ ምርመራው እንዳይጣራ ለፍ/ቤት በቃል አመልክቶ እንዲፈታ በማስደረጉ፣
- 4ኛ ተከሣሽ ምርመራ እንዲጣራ ትዕዛዝ ሰጥተው ለነበሩት ዐቃቤ ሕግ አቶ አምደሚካኤል ጌታቸው የስልክ ትዕዛዝ በመስጠት በ6ኛ ተከሣሽ ላይ ምርመራ እንዳይጀመር በማድረጉ፣
- 2ኛ ተከሳሽ 6ኛ ተከሣሽ በተጠረጠረበት ብልሹ አሰራርና የሙስና ወንጀል በባለሥልጣኑ ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37/1/ መሠረት የዲሲፒሊን እርምጃ እንድወሰድና ለሕግም እንዲቀርብ ማስደረግ ሲገባው በስራው ላይ እንዲቆይና በሕግም እንዳይጠየቅ በማድረጉ፤
- 6ኛ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ታስሮ ምርመራው የተጀመረበት ቢሆንም ከ2ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ምክንያት የነሱን ሽፋን ተጠቅሞ ምርመራው እንዲቋረጥለት በማስደረግ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሣሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
10ኛ ክስ
በ6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 413/1/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሹ በኢት/ገ/ጉ/ባለሥልጣን የአዋሽ መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት አስቦ በ8/8/2002 ዓ.ም ስሟ ለጊዜው ያልታወቀች ኮንትሮባንዲስት ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዝ ተሽከርካሪ ተሳፍራ ስትመጣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አዋሽ መቅረጫ ጣቢያ ላይ በተደረገባት ፍተሻ ሦስት ሶኒ ዲጅታል ካሜራ ተይዞባት በደረሰኝ ቁጥር 849781 ተመዝግቦ የነበረውን ደረሰኝ እንዲሰረዝ (void እንዲሆን) በማድረግና በማስደረግ ወስዶ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ በፈፀመው በሥራ ተግባር ላይ የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል ተከሷል።
11ኛ ክስ
በ6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 408(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የላጋር መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ በኃላፊነቱ እና በሥራ ግዴታው ማድረግ የማይገባውን በማድረግ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት አስቦ፤
- ቀኑ በውለ ተለይቶ ባልታወቀበት ጥር ወር 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 03 ፖሊስ መምሪያ አካባቢ ወደ ኮንደሚኒየም በሚወስደው መንገድ ላይ ኤምዲ (MD Transit) የተባለ ድርጅት አስተላላፊ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ታደሰ ገ/ዮሐንስ ላይ ከጅቡቲ ተጓጉዞ ድሬዳዋ ጉምሩክ የገባ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በሠነድ ከተዘረዘሩት በላይ (ትርፍ) በመገኘቱ ዕቃው በመያዙ ዕቃውን ለመልቀቅ ብር 10‚000 (አሥር ሺ ብር) ተቀብሎ በመውሰዱ፤
- ቀኖቹ በውል ተለይተው ባለታወቁበት በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም በተለያዩ ሁለት ቀናት ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን፤ በድሬዳዋ ከተማ 03 ቀበሌ ማርያም ሰፈር ዲፖ አካባቢ የንግድ ረዳት ሆነው ይሰሩ ከነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ከጅቡቲ ተጓጉዘው ድሬዳዋ ጉምሩክ የገቡ አምፖሎች ተፈትሸው ከተጠናቀቁ በኋላ ተከሳሹ ገንዘብ ካልሰጠኸኝ እቃዎቹ አይወጡም ብሎ በመደራደር ለመጀመሪያዎቹ ብር 15‚000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሁለተኛዎቹ ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ) በድምሩ ብር 35‚000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) ተቀብሎ በመውሰዱ፤ በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሷል።
12ኛ ክስ
በ2ኛ፣ 4ኛ እና 9ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣ 33፣ እና 408(1) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች እንደቅደም ተከተላቸው በኢትዮጰያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ዋና ዐቃቤ ሕግ ሆነው ሲሰሩ፣ በስራ ኃላፊነታቸው ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ፣ 9ኛ ተከሳሽ በበኩሉ የመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ አካፋይ በመሆን፤
- 2ኛ ተከሣሽ ብሥራት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተባለ ድርጅት ያለ ቫት ደረሰኝ ግብይት ሲፈፅም ተከሣሹ ለሚሰራበት መ/ቤት ጥቆማ ቀርቦ እንደ ጥቆማው አቀራረብ ለማረጋገጥ የድርጅቱ ሠራተኞች መጋቢት 29 ቀን 2001 ዓ.ም ወደ ድርጅቱ በመሄድ ኦፕሬሽን ሲካሄድ ያለደረሰኝ ግብይት እያከናወነ መሆኑ በመረጋገጡ በድርጅቱ፤ በድርጅቱ ባለቤትና ሌሎች ሁለት የድርጅቱ ሠራተኞች ላይ ምርመራ ተጣርቶ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ላይ እያለ ተከሣሹ ለብሥራት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ባለቤት አቶ ባህሩ አብርሃ በቀጥታ መስመር ስልካቸው ላይ በመደወል “አንተ ከማን ትበልጣለህ ወደ መደበኛ ፍ/ቤት ክስህን አቅርበን ከፍተኛውን ቅጣት አንደምናስቀጣህ እወቅ” በማለት ግለሰቡን በማስፈራራትና በማስጨነቅ በተከሳሹ የቅርብ አገናኝ በነበረው 9ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ቀጠሮ በማስያዝ ከላይ የተጠቀሰውን ባለሀብት ቢሮው በተደጋጋሚ እንዲገኝ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው የማስፈራሪያ ቃል በማስፈራራት “ሌሎች ልጆች ከእኔ ጋር ስላሉ በደንብ ተዘጋጅተህ ና” በማለት የራሱን ስልክ ቁጥር በመስጠት የስልክ ግንኙነት በማድረግ ቀኑና ወሩን በትክክል በማይታወቅበት 2004 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ዮርዳኖስ ሆቴል አካባቢ ከምሽቱ 1፡45 ሰዓት በመቅጠር ብር 250‚000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከባለሀብቱ ከተቀበለ በኋላ ባሀብቱ አድርጐት የነበረውን ብራስሌት እጁ ላይ ከተመለከተ በኋላ “የእሱ ዓይነት ግዛልኝ” በማለት ግለሰቡ በብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) የተገዛ ብራስሌት በማግስቱ ኢንተርኮንቴኔታል ሆቴል አካባቢ ድረስ ይዞ በመሄድ ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ ተከሳሹ በእራሱ መኪና ውስጥ ሆኖ ተቀብሎ ጉዳዩ እንዲጨርስለት ለ4ኛ ተከሣሽ ነግሮ ጉዳዩ እንዲያልቅ በማድረጉ፤
- 4ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ቀኑና ወሩን በውል በማይታወቅበት በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ፒያሣ ግራር ሆቴል እየተባለ ከሚጠራ ሆቴል ውስጥ በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ባለቤት (አቶ ባህሩ አብርሃ) ብር 50‚000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀኑና ወሩ በውል በማይታወቅበት ጊዜ ባለሀብቱን እቤቱ ድረስ በመጥራት ብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) እና ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ ብር) በአጠቃላይ ብር 100‚000 (መቶ ሺህ ብር) በመቀበሉ እና ከባለሀብቱ ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ተቀብሎ በባለሀብቱ ላይ የተመሠረተውን ክስ በፍ/ቤት በነፃ ከተሰናበተ በኋላ ይግባኝ እንይጠየቅ በማድረጉ፤
- 9ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ቀኑና ወሩ በማይታወቅ በ2004 ዓ.ም ባህሩ አብርሃ የተባሉ የብሥራት ኃ/የተ/ማኅበር ባለቤት በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተመሰረተባቸውን ክስ እንዲዘጋ ከ2ኛ ተከሣሽ ጋር በማገናኘት ብር 250‚000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና ብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) የሚያወጣ ብራስሌት 2ኛ ተከሣሽ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲያገኝ በማድረጉ፤
በአጠቃላይ ተከሣሾች በመላ ሀሳባቸውና አድራጐታቸው በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተከፋይ በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
13ኛ ክስ
በ2ኛ፣ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 419(1) (ሀ) እና ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
2ኛ ተከሳሽ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ እጁ እስከተያዘበት 2005 ዓ.ም ተቀጥሮና ተሹሞ ሲሰራ ከብር 247 (ሁለት መቶ አርባ ሰባት) እስከ ብር 5‚700 (አምስት ሺህ ሰባት መቶ) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው እንደነበረ እና 13ኛ ተከሣሽ ደግሞ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር ከ01/11/1989 ዓ.ም እስከ 30/01/2000 ዓ.ም ተቀጥራ ስትሰራ ከብር 790 (ሰባት መቶ ዘጠና ብር) እስከ ብር 2‚145 (ሁለት ሺህ አንድ መቶ አርባ አምስት) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላት የነበረ ሲሆን ተከሳሾቹ ያገኙት ከነበረው ደመወዝና ገቢ ጋር የማይመጣጠን፤
1ኛ. በወጋገን ባንክ ካዛንቺስ አካባቢ በሂሣብ ቁጥር 302993 ብር 96‚477.79 (ዘጠና ስድስት ሺ አራት መቶ ሰባ ሰባት ከሰባ ዘጠኝ ሣንቲም) በ13ኛ ተከሳሽ ስም
2ኛ. በእናት ባንክ እቴጌ ጣይቱ አብይ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር R/S746 ብር 4‚000 (አራት ሺህ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
3ኛ. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 1000001730766 ብር 1‚427.59 (አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሰባት ከሃምሳ ዘጠኝ ሳንቲም) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
4ኛ. በኢትዮጰያ ልማት ባንክ በሂሣብ ቁጥር 1258hA, 40612HC, 35933HD, 41304HE, 2636HG, ብር 3‚925 (ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
5ኛ. የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤ.ቁ. 634 የካርታ ቁጥር 29870 የቦታው ስፋት 4‚000 ካ.ሜ የሆነ ቦታ ተከሣሽን ጨምሮ 7 ሰዎች በብር 4‚200‚000 (አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር) የተገዛ ቦታ (የተከሳሽ ድርሻ ብር 600‚000 (ስድስት መቶ ሺህ ብር)፤
6ኛ. የሠሌዳ ቁጥር 3-02725 ትግ የሆነ አውቶቡስ ተሽከርካሪ (ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
7ኛ. የሠሌዳ ቁጥር 3-49614 አ.አ የሆነ የንግድ መኪና (ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
8ኛ. የካረታ ቁጥር 2713/22/93 መቀሌ ከተማ ቀበሌ 11 የሚገኝ መኖሪያ ቤት በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
9ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም ዳሸን ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 5013022467001 ብር 42244.62፣
10ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም አንበሳ ባንክ የካ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 00300000799-97 ብር 387.65
11ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም ወጋገን ባንክ መስቀል ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 23444/501/03024 ብር 102‚553.50 (አንድ መቶ ሁለት ሺ አምስት መቶ ሃምሳ ሦስት ከ50/100)
12ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) ካሳንቺስ ቅርንጫፈ በሂሳብ ቁጥር 262179 ብር 18‚142.04፣
13ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) ካሳንቺስ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 262180 ብር 1‚015.07፣
14ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ቅርንጫፈ በሂሳብ ቁጥር 1000013401587 ብር 1‚753.77፣
15ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 0173007267000 ብር 203424.99 (ሁለት መቶ ሦስት ሺ አራት መቶ ሃያ አራት ከ99/100)፤
16ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም በአንበሳ ባንክ የብር 34‚275.25 (ሰላሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ሰባ አምስት ከ25/100) አክስዮን፤
17ኛ. በሳሙኤል ገ/ዋህድስም (ልጅ) የብር 10‚000 (አሰር ሺ) አክስዮን፤
18ኛ. ከተከሳሾች መኖሪያ ቤት የተገኘ፡-
18.1. የኢትዮጵያ ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺ)
18.2. EURO 19435 (አስራ ዘጠኝ ሺ አራት መቶ ሰላሳ አምስት)
18.3. USD 26300(ሃያ ስድስት ሺ ሶስት መቶ)
18.4. POUND 560 (አምስት መቶ ስድሳ)
18.5. TAILAND 210 (ሁለት መቶ አስር)
19ኛ/ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139100 ግምቱ ብር 596868፣24 የሆነ 500 ካ.ሜ
20ኛ/ 6 የተለያዩ ላፕቶፖች፤
በአጠቃላይ ተከሳሾች የኑሮ ደረጃቸው አሁን ባለበትም ሆነ አስቀድሞ በነበሩት የመንግሥት ሥራ ከሚያገኙት ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን ብር 1,451,941.609 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ከ60/00)፣ ከላይ ከተራ ቁጥር 18.2 – 18.5 ድረስ የተጠቀሱትን የውጭ አገር ገንዘቦችና እና እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶች ይዘው በመገኘታቸው በፈፀሙት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
14ኛ ክስ
በ2ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 684(1) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በ13ኛው ክስ በተገለፀው ጊዜና አኳኋን በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ያገኙትን ገንዘብና ንብረት ህገወጥ አመጣጡን በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ በማሰብ መሬት እና መኪና በመግዛት፣ በተለያዩ ባንኮች በእራሳቸውና በልጆቻቸው ስም እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ገንዘቦችን በማስቀመጥ በፈፀሙት በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
15ኛ ክስ
በ13ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 40፣419 እና 684 ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፏ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሿ ባለቤቷ የሆነው 2ኛ ተከሳሽ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን የወንጀል ፍሬ መሆናቸውን እያወቀች ባለቤቷ በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ከመከሰስና ከመቀጣት እንዲያመልጥ ለመርዳት፡-
1. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል ስም ተመዘገበ የባንክ ደብተር ቁጥር 0123586 የሆነ ብር 10000 (አስር ሺ) ተቀማጭ ያለው፤
2. ካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139/00/06/01 ከለገጣፎ ለገዳዲ አስተዳደር ለገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠ፤
3. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እና በወ/ሮ ሀይማኖት ተስፋዬ ስም ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ብር 820,000 (ስምንት መቶ ሃያ ሺ ብር) ብድር ለመጠየቅ የተሞላ ቅፅ፤
4. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እና በኮ/ል ሃይማኖት ተስፋዬ ስም ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) የባንክ ሼር ለመግዛት የጠየቁበት ሰነድና የተለያዩ የቤት ፕላኖችን ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እህቷ ለሆነችው ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋ ገ/ስላስ እና አቶ ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ ለተባሉ ግለሰቦች አሳልፋ በመስጠትዋ በፈፀመችው ወንጀል ከተፈፀመ በኋላ ወንጀል አድራጊውን መርዳት ወንጀል ተከሳለች።
16ኛ ክስ
በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን ኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 808(ሀ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ደንብ ተከትሎ ፈቃድ ከሚሰጥ አካል አስፈቅዶ መያዝና መጠቀም ሲገባው ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ሳያስፈቅድ የመኖሪያ ቤቱ በ02/09/05 ዓ.ም በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ብርበራ በተካሄደበት ወቅት፡-
1. የውግ ቁጥር 1529 የሆነ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ፣
2. የውግ ቁጥር 0624 የሆነ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ፣
3. የውግ ቁጥር ሠበ0402 የሆነ ማክሮቭ ሽጉጥ
4. የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ፣
5. የውግ ቁጥር የሌለው ኮልት ሽጉጥ፣
6. የውግ ቁጥር 47391 ኮልት ሽጉጥ፣
7. የውግ ቁጥር NK252926 ማካሮቭ ሽጉጥ፣
8. የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ
9. የውግ ቁጥር 2235 ስታር ሽጉጥ እና
10. የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ
በፈፀመው እንዲይዝ ያልተፈቀደለትና ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል።
17ኛ ክስ
በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 419(1)(ለ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ በሰራበት ከ22/11/87 ዓ.ም እስከ 30/7/2004 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ተቀጥሮ ሲሰራ በወር ይከፈለው የነበረው ያልተጣራ ደሞዝ ከብር 445 (አራትመቶ አርባ አምስት) እስከ ብር 8,651 (ስምንት ሺ ስድስትመቶ ሃምሳ አንድ ሺህ) ሲሆን በመንግስት ስራ ላይ እያለ ያገኝ ከነበረው ከህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን፡-
1ኛ/ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በመኖሪያ ቤቱ ብርበራ ተደርጎ የተገኘ ብር 1,947,676.10 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/፣
2ኛ/ በተለያዩ ባንኮች እና የአክሲዮን ማህበራት በተከሳሽ ስም የተቀመጠ በድምሩ ብር 2,090,880.03 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኛ ሺ ስምንተ መቶ ሰማንያ ብር ከአስር ሳንቲም/
3ኛ/ በተከሳሽ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/
4ኛ/ በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 24፣ ቀበሌ 02/03 በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ተመዘግቦ የሚገኝ 74.56 ካ/ሜ ስፋት ላይ የተሰራና ግምቱ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሆነ ባለ ሁለት መኝታ ኮንደምኒየም ቤት፣
5ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም በተለያዩ ባንኮች የተቀመጠ በድምሩ ብር 185,641.19 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አንድ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም/
6ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም አክሲዮን የተገዛበት ብር 5,000፣ አምስት ሺህብር/፣
7ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣
በአጠቃላይ ተከሳሹ በስሙና በባለቤቱ ስም ብር 4,459,197.5 /አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ የሆነ ከፍተኛ ንብረትና ገንዘብ በመያዝ የኑሮ ደረጃው የማይፈቅድለትን ሀብት አከማችቶ በመገኘቱ በፈፀመው ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
18ኛ ክስ
በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 684(1) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ17ኛው ክስ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኋን በፈፀመው በሙስና ወንጀል ያገኘውን ገንዘብና ንብረት ህገወጥ አመጣጡን በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ በማሰብ፣
1ኛ/ በመኖሪያ ቤቱ ብርበራ ተደርጎ የተገኘ ብር ብር 1,947,676.10/ አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/
2ኛ/ በተለያዩ ባንኮች እና የአክሲዮን ማህበራት በተከሳሽ ስም የተቀመጠ በድምሩ ብር 2,090,880.03 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠና ሺህ ስምንተ መቶ ሰማንያ ብር ከአስር ሳንቲም/
3ኛ/ በተከሳሽ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣
4ኛ/ በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 24፣ ቀበሌ 02/03 በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ 74.56 ካ/ሜትር ስፋት ላይ የተሰራና ግምቱ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሆነ ባለ ሁለት መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት፣
5ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም በተለያዩ ባንኮች የተቀመጠ በድምሩ ብር 185,641.19 /አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርበ አንድ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም/
6ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም አክሲዮን የተገዛበት ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/
7ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ህጋዊ አስመስሎ ይዞ በመገኘቱ በፈፀመው በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሷል።
19ኛ ክስ
በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ2002 ዓ.ም በስራ ላይ የዋለውን ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 668/2002 አንቀጽ 22/1/ሀ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ17ኛ ክስ በተጠቀሰው ስራ ኃላፊነት ተመድቦ ሲሰራ በራሱና በባለቤቱ ስም የሚገኘውን ሀብት የማስመዝገብ ግዴታ እያለበት በ17/08/03 ዓ.ም ለፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሀብትማሳወቂያና ማስመዝገቢያ ዳይሬክቶሬት ሲያስመዘግብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በ02/09/05 ዓ.ም በተደረገ ብርበር የተገኘውን ብር 1,947,676.10 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/ ሳያስመዘግብ፣ በስሙና በባለቤቱ ስም በተለያዩ ባንኮች እና የአክስዮን ማህበራት ያስቀመጠውን የገንዘብ መጠን ቀንሶ በማስመዝገብ እና ደብቆ ይዞ የተገኘበት በመሆኑ ማሳወቅ የሚገባውን ሀብት ባለማሳወቅና ባለማስመዝገብ ወንጀል ተከሷል።
20ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 419/1/ሀ/እና /ለ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ1/5/87 ዓ.ም ጀምሮ እጁ እስከተያዘበት እስከ ግንቦት 3 ቀን 2005 ዓ.ም ተቀጥሮ ሲሰራ ከብር 2535 (ሁለት ሺ አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር) እስከ ብር 10234 (አስር ሺህ ሁለትመቶ ሰላሳ አራት ብር) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው የነበረ ሲሆን ተከሳሹ ያገኘው ህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን ፣
1ኛ/ በ30/09/2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በተደረገ ብርበር በኤግዚቢትነት ተመዝግቦ የሚገኝ ጥሬ ብር 1,388,899 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር)
2ኛ/ እ.ኤ.አ ከ4/8/2012 እስከ 19/06/2013 ባለው ጊዜ የቤት እመቤት በሆነችው ባለቤቱ ወ/ሮ ካሰች አምደመስቀል መገርሳ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጦር ኃይሎች ቅርንጫፍ የሚገኝ ብር 907,633.62 (ዘጠኝ መቶ ሰባት ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ62 /100 ሳንቲም)
3ኛ/ ከ2002 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ገንዘብ መጠን ይዞ እየተመላለሰ “ውጭ ሀገር የሚገኙ ጓደኞቼ የላኩልኝ ገንዘብ ነው አንቺ ጋር ይቀመጥልኝ” በማለት በሀሳዋ ከተማ አላሙራ ክ/ከተማ ጉዮ ቀበሌ ነዋሪ ከሆነችው እህቱ ወ/ት ትእግስት አለማየሁ ድረስ በመሄድ በድምሩ ብር 1,900,000.00 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) እሷ በከፈተችው አካውንት እንዲቀመጥ በማድረጉ፤
4ኛ/ በተለያዬ ወቅት ለእህቱ ትእግስት አለማየሁ ገንዘብ በመስጠት በአዋሳ ከተማ አላሙራ ክ/ከተማ በተለምዶ ዲያስፖራ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ግምቱ ብር 1,425,000 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ አምስት ሺ) የሚያወጣ መኖሪያ ቤት በስሟ በማሰራቱ፣
5ኛ/ በሃሳዋ ከተማ መናኸሪያ ክ/ከተማ የቦታ መለያ ቁጥር APR-95 59 የፋይል ቁጥር 1595/1737 የቦታው ስፋት 275 ካ.ሜ በሆነው ቦታ የገቢ ምንጩ ሊያሰራው የማይችለውን ቤት ሰርቶ ሚያዝያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ የቤት ሽያጭ ብር 930,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺ ብር) በማስተላለፉ፣
በአጠቃላይ ተከሳሹ ከሚያገኘው የደመወዝ ገቢ ጋር የማይመጣጠን በድምሩ ብር 6,551,532.62 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ አምስትመቶ ሰላሳ ሁለት ብር ከስድሳ ሁለት ሳንቲም) ገንዘብ አካብቶ በመገኘቱ በፈፀመው ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ አካብቶ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
21ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 684(1) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ20ኛው ክስ የተገለፀውን በሙስና ያገኘውን ንብረትና ገንዘብ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ምንጩን ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን እና የንብረቱን ሕገወጥ አመጣጥ በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ አስቦ፣ በራሱ ስም ቤት ሰርቶ በውክልና ስም በእጅ አዙር በማሸጥ፣ በእህቱ ትእግስት አለማየሁ ስም ቤት በማሰራት እና ገንዘብ በማስቀመጥ ፣ በባለቤቱ ስም በተከፈተ አካውንት ገንዘቡ እንዲቀመጥ በማድረግ እንዲሁም፣ በሚስጥር ገንዘቡን ወደ ወላይታ ሶዶ ዞን ሶዶ ወረዳ ላሾ ቀበሌ ከሚገኘው ወንድሙ አቶ ብርሃኑ አለማየሁ ዘንድ መኖሪያ ቤታቸው በመላክ መሬት ውስጥ እንዲቀበር በማድረጉ በፈፀመው በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሷል።
22ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 407/1/ሀ/እና /ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዐቃቤ ህግ ሲሆን የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ ሂልቦቶም የመዝናኛ ማዕከል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሐምሌ እና ነሀሴ 2001 ዓ.ም የሚፈለግበትን የተርን ኦቨር ታክስ እንደከፈለ በማስመሰል ቁጥራቸው 1398705002 የሆኑ ሁለት ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ሀሰተኛ የተርን ኦቨር ታክስ መሰብሰቢያ ደረሰኞች በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም ለኢት/ገ/ጉ/ባለሥልጣን ምሥራቅ ቅ/ጽ/ቤት በማቅረቡ በፈፀመው ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል በድርጅቱ፣ በድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እና በፋይናንስ አስተዳደር ሠራተኞች ላይ በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ እለ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ተከሳሾቹ ከህግ ተጠያቂነት እንዲያመልጡ እርምጃም እንዳይወሰድባቸው ለማድረግ በቁጥር 5.2.2/2412/80 በ24/8/2004 ዓ.ም በፍ/ቤቱ በፃፈው ማመልከቻ ክሱ አለአግባብ እንዲነሳ በማድረጉ በፈፀመው በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል።
23ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የገንዘብና የባንክ አዋጅ ቁጥር 83/1986 አንቀጽ 59(1) (ሸ) ስር የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ አሜሪካ አገር ከምትኖረው ትእግስት ከተማ ከበደ ከተባለች ልጁ ውክልና በመውሰድ ጌታነህ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ዮሐንስ ጌታነህ ካሳ ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ስምምነት ብር 40,000,000 (አርባ ሚሊዮን ብር) ብድር በመስጠት ለባንኮችና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ብቻ የተፈቀደውን የባንክ ስራ በህገወጥ መንገድ እንደ ንግድ ስራ ሲሰራ በመገኘቱ በፈፀመው ወንጀል ተከሷል።
24ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 715(ሀ) እና (ሐ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ አቶ ዮሀንስ ጌታነህ ካሳ የተባሉ የግል ተበዳይን የገንዘብ ችግር መሰረት በማድረግ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር ጣና ቅርንጫፍ እና ከአቢሲኒያ ባንክ ነጋድራስ ቅርንጫፍ ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከግል ተበዳይ ድርጅት በተለያዩ ቀናት በተፃፉ የተለያ ቼኮች በልጁ ትእግስት ከተማ ከበደ፣ በእራሱ በተከሳሹ እና ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተባለ በእራሱ ድርጅት በህግ ከተፈቀደው ወለድ በላይ ብር 111,705,397.83 (አንድ መቶ አስራ አንድሚሊዮን ሰባት መቶ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር 83/100 ሳንቲም) አራጣ በማስከፈል በግል ተበዳይ ላይ የሀብት መራቆት እንዲደርስበትና እራሱን እንዲያጠፉ በማድረጉ በከባድ ሁኔታ አራጣ ማበደር ወንጀል ተከሷል።
25ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀል
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 407/1/ሀ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዐቃቤ ህግ ሲሆን የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት እንዲሁም በሌላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ኢኖቫ ፖሊባግ ኃ/የተ/የግ/ማ እ.ኤ.አ ከ2005 እስከ 2009 የገቢ ግብር ብር 16,099.26 (አስራ ስድስት ሺህ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከሃያ ስድስት ሳንቲም፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 52,679.93 /ሃምሳ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) አለመክፈሉ በወንጀል ምርመራ መዝገብ ተጣርቶ ዐቃቤ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ እያለ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እና ድርጅቱ በፍ/ቤት እንዳይቀጡ ለማድረግ እንዲሁም በቀረበው የምርምራ መዝገብ ያልተሸፈነ ተጨማሪ ዕዳ ያለበት መሆኑ እየተገለፀለት ባለበት ሁኔታ ምርመራው እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ለምርመራ ክፍሉ ሲያስተላልፍ የባለሥልጣኑ የምርመራ ክፍሉም ክስ መቅረብ ሲገባው መቋረጡ ተገቢ አይደለም፣ ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ እንዲወሰን፣ ቢጠይቅም በድጋሚ በቁጥር 5.2.2/5978/1993 መጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ለባለሥልጣኑ ወንጀል ምርመራ ቡድን በፃፈው ደብዳቤ ምርመራው እንዲቋረጥ በማድረጉ በፈፀመው በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል።
26ኛ ክስ
በ2ኛ ፣ 4ኛ፣ 14ኛ እና 15ኛ ተከሳሾች ላይ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና 408 (1) ላይ የተመለከተውን በመተላፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች በክሱ በተከሳሾች ዝርዝር ውስጥ በተጠቀሰው ኃላፊነት ሲሰሩ በሥራ ኃላፊነታቸው ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ የባለሥልጣኑ ግብር ከፋይ የሆነውን ኦፊስ ቴክ ኃ/ተ/የግል ማህበር ባለቤት አቶ መሀመድ ዩሱፍን ድርጅቱ ኦዲት በሚደረግበት፣ በታክስ ማጭበርበር በወንጀል ከመከሰሱ በፊትና ከተከሰሰም በኋላ በ2002 እና በ2003 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ በማግኘት፣
14ኛ ተከሳሽ በ2002 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ በተለያዩ ቀናት ውስጥ የግል ተበዳዩን ተከታትሎ ካገኘው በኋላ “የላከን ገብረዋህድ ነው የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን አንተን እንድንቀጣላቸው ይፈልጋሉ። ስለዚህ ሁለት ሚሊዮን ብር አምጣ ካልሆነ ግብርም ይጨመርብሃል፤ አንተም ትታሰራለህ” በማለት የግል ተበዳይ ጉቦ እንዲሰጠው በአካልና በስክል በመጠየቁ፣ በመቀጠልም የግል ተበዳይ ወደ ዱባይ ሀገር በሄደበት ወቅት አብሮ እንዲሰራ የተመደበውን ኦዲተር ትቶ ብቻውን ወደ ግል ተበዳይ ድርጅት በመግባት በአንድ ቀን ውስጥ የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት አድርጎ አርባ ሁለት ሚሊዮን ብር በማምጣት በድርጅቱ ውስጥ በተለማማጅነት የምትሰራውንና የመፈረም ሥልጣን የሌላትን 2ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክርን አስፈራርቶ በማስፈረሙ፣
2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ በ2003 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የግል ተበዳይ ግብር ዜሮ እንዲሆንለት የወንጀል ክሱም እንዲቋረጥለት ሁለት ሚሊዮን ብር እንዲከፍል፣ ይህንንም ገንዘብ ዱባይ ሀገር በሚገኝ ሰው አማካኝነት እንዲያስገባ በተደጋጋሚ ጊዜ 14ኛ ተከሳሽንና ሌሎችንም የግል ተበዳይ አዲስ አበበ ውስጥ ኦሎምፒያ በሚባለው አካባቢ ያገኛቸው ሶስት ደላሎችን በመላክ ጉቦ በመጠየቁ፣ በማግስቱም የግል ተበዳይ ሁኔታውን ለማጣራት ፈልጎ ተከሳሹ ቢሮ ሲሄድ ተከሳሹ እንዲገባ ከፈቀደለት በኋላ የግል ተበዳይን “አንተ አመፀኛ ይህ የከተማ ጮሌነት ከአንተ በላይ አውቀዋለሁ። ኦሎምፒያ አካባቢ ከቀጠሩህ ሰዎች ጋር ጨርስ” በማለት የግል ተበዳይን በማስፈራራት በቀጥታ ገንዘቡን እንዲከፍል በመጠየቁ፣
4ኛ እና 14ኛ ተከሳሾች በበኩላቸው የግል ተበዳይ ላይ ክስ ቀርቦበት በሂደት ላይ እያለ የፍ/ቤት ቀጠሮ ለማራዘምና ለተከሳሹ ጊዜ ለመስጠት በሚል በ4ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር አማካኝነት ጉቦ እንዲሰጣቸው በመጠየቅና በመደራደር ሁለት ቶሺባ ላፕቶፕ፣ ሁለት ሲዲኤምኤ እና ብር 20,000 (ሃያ ሺ) ቀኑ ባልታወቀ መስከረም ወር 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ኒዎርክ ካፌ ተቀብለው በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው፣
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በግል ተበዳይ የሚተዳደረው ኦፊስቴክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተባለው ድርጅት ኦዲት ከመደረጉ በፊትና ከተደረገም በኋላ እንዲሁም የግል ተበዳይ ላይ የወንጀል ክስ ከመቅረቡ በፊትም ሆነ ከቀረበበት በኋላ የግል ተበዳዩ ግብር እንዲቀነስለት የወንጀል ተጠያቂነትም እንዳይመጣበት ለማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ 2ኛ እና 14ኛ ተከሳሾች የግል ተበዳይ ጉቦ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው፣ 4ኛ እና 15ኛ ተከሳሾች ደግሞ ጉቦ በመቀበላቸው ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ጉቦ መጠየቅና መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
27ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 32,217,578.36 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከ36/100 ሳንቲም) ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አስታውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
28ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሰቴ ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56(1) እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ18ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 27ኛ ክስ የተመለከተውን ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
29ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 50(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ27ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለሥልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 32,217,578.36 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከ36/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
30ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 56(1)፣50(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ18ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 29ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
31ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 17,869,941.49 (አስራ ሰባት ሚሊዮን ስምነት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ብር ከ49/100 ሳንቲም) ለመንግሥት አስታውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
32ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102(1) እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ18ና ተከሳሽ ላይ በቀረበው 31ኛ ክስ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
33ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1004 አንቀጽ 97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመስራት ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት በአጠቃላይ ብር 17,869,941.49 (አስራ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ብር ከ49/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
34ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 አንቀጽ 102(1)፣97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ18ና ተከሳሽ ላይ በቀረበው 33ኛ ክስ የተመለከተውን አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
35ኛ ክስ
በ10ኛ እና 18ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1) (ሀ) (3) እናየጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 93(1)(ሀ)2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ያስገቧቸው የተለያዩ ዕቃዎች በህጉ በተቀመጠው የእቃዎች የታሪፍ አመዳደብና የዋጋ ተመን መሰረት ክፍያ መክፈል ሲገባቸው ከህግና ከመመሪያ ውጭ በመስተናገድ ብር 9,543,391.45 በማጭበርበር ያለአግባብ ተጠቃሚ በመሆናቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የማጭበርበር ወንጀል ተከሰዋል።
36ኛ ክስ
በ10ኛ እና በ18ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(3)፣ 684(1)(2)(6) እና (7) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግሥት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 32,217,578.36 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከ36/100 ሳንቲም)፣ የገቢ ግብር 17,869,941.49 (አስራ ሰባትሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ብር ከ49/100 ሳንቲም)፣ ከገቢ ዕቃዎች ብር 9,543,391.45 (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሺ ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ከ30/100 ሳንቲም) ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
37ኛ ክስ በ19ና ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግሥት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 20,111,328.94 (ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ94/100 ሳንቲም) ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
38ኛ ክስ በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56(1) እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 37ኛ ክስ የተመለከተውን ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
39ኛ ክስ
በ19ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50(1) እና 3(ለ) ላይ ተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ37ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለሥልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 20,111,328.94 (ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ49/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልጽ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
40ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56(1)፣ 50(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 39ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተሰኳል።
41ኛ ክስ
በ19ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 29,433,214.24 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ብር ከ24/100 ሳንቲም) የገቢ ግብር እና በግዥና እቃ አቅርቦት ውል ከሚፈፀም ክፍያ ብር 632,860.27 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስልሳ ብር ከ27/100 ሳንቲም) ለግብር አስገቢው ባለስልጣን ገቢ ባለማድረጉና አስታውቆ መክፈል የሚገባውን ግብር አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
42ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 102(1) እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 41ኛ ክስ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
43ኛ ክስ
በ19ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1991 አንቀጽ 97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመሥራት ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት የንግድ ትርፍ ግብር ብር 29,433,214.24 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ብር ከ24/100 ሳንቲም) እና በግዥና እቃ አቅርቦት ውል 632,860.27 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስልሳ ብር ከ27/100 ሳንቲም) በድምሩ 30,263,641.12 (ሰላሳ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አንድ ብር ከ12/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
44ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 አንቀጽ 102(1)፣97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 43ኛ ክስ የተመለከተውን አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ሰራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
45ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ2001 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 98(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በ19ኛ ተከሳሽ ስም የቀረጥ ነፃ መብት በመጠቀም ወደ ሀገር የገቡ የቀረጥና ታክስ መጠናቸው ብር 197,556.61 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከ61/100 ሳንቲም የሆኑ ለኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ኪራይ ፕሮጀክት አገልግሎት እንዲያውል ከቀረጥ ታክስ ነፃ ተፈቅዶለት እያለ ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ ለሆቴል ማስፋፊያ ስራ በማዋሉ በፈጸመው ከቀረጥ ነፃ የገባን ዕቃ አላግባብ መገልገል ወንጀል ተከሷል።
46ኛ ክስ በ11ኛ እና በ19ና ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(3)፣ 684(1)(2)(6) እና (7) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግሥት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 20,111,328.94 (ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ94/100 ሳንቲም)፤ የንግድ ትርፍ ግብር ብር 29,433,214.24 ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ብር ከ24/100 ሳንቲም፤ በግዥና እቃ አቅርቦት ውል ከሚፈፀም ክፍያ ላይ ሁለት በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሶ ማስቀረት ሲገባው ብር 632,860.27 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስልሳ ብር ከ27/100 ሳንቲም) እና በ19ኛ ተከሳሽ ስም የቀረጥ ነፃ መብት በመጠቀም ወደ ሀገር የገቡ የቀረጥና ታክስ መጠናቸው ብር 197,556.61 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከ61/100 ሳንቲም) የሆኑ ለኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ኪራይ ፕሮጀክት አገልግሎት እንዲያውል ከቀረጥ ታክስ ነፃ ተፈቅዶለት እያለ ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ ለሆቴል ማስፋፊያ ስራ በማዋሉ በድምሩ ብር 50,374,960.06 (ሃምሳ ሶስት መቶ ሰባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ብር ከ06/100 ሳንቲም) ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
47ኛ ክስ
በ9ኛ፣ 16ኛ፣ 17ኛ፣ ከ20ኛ–22ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የጉምሩክ ባለስልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀፅ 64/3(ሀ) እና (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾች እንደቅደምተከተላቸው በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው የ20ኛ፣ 21ኛ እና 22ኛው ተከሳሾች ባለቤትና ስራ አስኪያጆች ሲሆኑ ከ1999 ዓ.ም እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በፍራንኮቫሉታ /ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት/ ከውጪ አገር በጂቡቲ በኩል 9ኛ እና 20 ተከሳሾች 13150 ኩንታል ሲሚንቶ፣ 16ኛ እና 21 ተከሳሾች 9000 ኩንታል ሲሚንቶ 17ኛ እና 22 ተከሳሾች 28980 ኩንታል ሲሚንቶ በየራሳቸው የትራንስፖርት ድርጅቶች በማጓጓዝ ካስገቡ በኋላ በገቡት ኃላፊነት መሰረት ያስገቡትን ሲሚንቶ በሙሉ ለተጠቃሚው አካል ማስረከብ ሲገባቸው በገበያ ላይ ለሽያጭ ለማዋል እንዳልሆነ እያወቁ የጉምሩክ ስነ ሥርዓት ባልተፈጸመበት መንገድ በመጠቀም ከታለመለት አላማ ውጪ 9ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች 18950 ኩንታል ሲሚንቶ፣ 16ኛው እና 21ኛው ተከሳሾች 8540 ኩንታል ሲሚንቶ፣ 17ኛው እና 22ኛው ተከሳሾች 17020 ኩንታል ሲሚንቶ ለ3ኛ ወገን በማስተላለፋቸው ሁሉም ተከሳች በፈፀሙት የማጓጓዝ ኃላፊነት ግዴታን በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል።
48ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፤
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,490,103.97 /አንድ ሚሊዮን አራ መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ዘጠና ሰባት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
49ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ48ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዋል።
50ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥረ 286/94 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,490,103.97 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ዘጠና ሰባት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
51ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 102/1/፣ 97/1 እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ50ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
52ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 5,093,734.61 /አምስት ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከስልሳ አንድ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
53ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ52ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሰዋል።
54ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፤
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 5,093,734.61 /አምስት ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከስልሳ አንድ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
55ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ54ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
56ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በተመላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛ በቀረበው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 5,489,670.63 /አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንለያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ብር ከስልሳ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
57ኛ ክስ
በ16ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ56ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዋል።
58ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 5,489,670.63 /አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ብር ከስልሳ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
59ኛ ክስ
በ16ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/፣ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ58ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
60ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁር 285/94 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 17,328,345.99 /አስራ ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
61ኛ ክስ
በ16ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ60ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሰዋል።
62ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 17,328,345.99 /አስራ ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
63ኛ ክስ
በ16 ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ62ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀሉ ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
64ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,461,331.13 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከአስራ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
65ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ64ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዋል።
66ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁር 286/94 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,461,331.13 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከአስራ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
67ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/፣ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ66ኛ ክስ ላይ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ ተከሷል።
68ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 4,902,285.69 /አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ብር ከስልሳ ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
69ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ68ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የደርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሰዋል።
70ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 4,902,285.69 /አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ብር ከስልሳ ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
71ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ70ኛ ክስ ላይ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ ተከሷል።
72ኛ ክስ
በ9ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ስራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/3/፣ 684/1/2/6 እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት 48ኛ እና 52ኛ ክሶች በተጠቀሱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸውን ግብር 1,490,103.97 ብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 5,093,734.61 ብር በድምሩ በር 6,583,838.558 /ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሃምሳ ስምንት ሳንቲም/ የሆነውን የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብለና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
73ኛ ክስ
በ16ኛ እና 21ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ስራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1//ሀ/3/፣ 684/1/2/6 እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት 56ኛ እና 60ኛ ክሶች በተጠቀሱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸውን ግብር 5489670 ብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 17,328,345.99 ብር በድምሩ ብር 22,818,016.62 /ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ አስራ አድስት ብር ከስልሳ ሁለት ሳንቲም/ የሆነውን የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
74ኛ ክስ
በ17ኛ እና 22ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ስራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/3/፣ 684/1/2/6 እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት 64ኛ እና 68ኛ ክሶች በተጠቀሱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸውን ግብር 1,461,331.13 ብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 4,902,285.69 ብር በድምሩ ብር 6,363,616.82 /ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አስራ ስድስት ብር ከሰማንያ ሁለት ሳንቲም/ የሆነውን የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
75ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 37,895,645.90 /ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ90/100 ሳንቲም/ ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አስታውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
76ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 75ኛ ክስ የተመለከተውን ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
77ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ75ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 37,895,645.90 /ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ90/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
78ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 77ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
79ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 32,666,482.23 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ23/100 ሳንቲም/ ለመንግስት አስታውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
80ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 79ኛ ክስ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
81ኛ ክስ
በ20 ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመስራት ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት በአጠቃላይ ብር 32,666,482.23 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ23/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
82ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 81ኛ ክስ የተመለከተውን አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
83ኛ ክስ
በ9ኛ እና በ20ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/3/፣ 684/1/2/6/ እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግስት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 37,895,645.90 /ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ90/100 ሳንቲም/፣ የገቢ ግብር 32,666,482.23 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ23/100 ሳንቲም/ በድምሩ ብር 70,562,128.23 /ሰባ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ስምንት ከ23/100 ሳንቲም/ ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብለና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
84ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 1,384,683.67 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ67/100 ሳንቲም/ ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አስታውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
85ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ84ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 1,384,683.67 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ67/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባ ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
86ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 3,859,605.26 /ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አምስት ብር ከ20/100 ሳንቲም/ ለመንግሥት አስታውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
87ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመስራት ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት በአጠቃላይ ብር 3,859,605.26 /ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አምስት ብር ከ26/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
88ኛ ክስ
በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 684/1/ እና 7/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግስት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 1,384,683.67 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ67/100 ሳንቲም/፤ የገቢ ግብር ብር 3,859,605.26 /ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አምስት ብር ከ26/100 ሳንቲም/ ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በማቅረቡ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀመው ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሷል።
89ኛ ክስ በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 417/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ በለገጣፎ ከተማ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139/00 በስሙ ተመዝግቦ በሚገኘው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ላይ የመኖሪያ ቤት ዲዛይን እንዲያሰራለት 23ኛ ተከሳሽን በመጠየቅ ተከሳሹም በጥያቄው መሰረት የመኖሪያ ቤት ዲዛይኑን በማሰራት ዲዛይኑ የተሰራበትን የአገልግሎት ዋጋ በድምሩ ብር 23,000.00 /ሃያ ሶስት ሺህ/ እ.ኤ.አ በ18/10/2012 እና በ06/04/2013 ለተከሳሹ የከፈለለትና ተከሳሹም ይህንኑ ጥቅም ያለምንም ክፍያና ተገቢ ምክንያት የተቀበለ በመሆኑ በፈፀመው ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
90ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 428 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በ89ኛ ክስ ላይ በተመለከተው ሁኔታ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ለሆነው 2ኛ ተከሳሽ በለገጣፎ ከተማ በስሙ ተመዝግቦ በሚገኘው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ላይ የመኖሪያ ቤት ዲዛይን እንዲያሰራለት በጠየቀው መሰረት የመኖሪያ ቤት ዲዛይኑን ካሰራለት በኋላ ዲዛይኑ የተሰራበትን የአገልግሎት ዋጋ በድምሩ ብር 23,000.00 /ሃያ ሶስት ሺህ/ በራሱ ወጪ የከፈለለት በመሆኑ በፈፀመው ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
91ኛ ክስ በ24ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 808/ሀ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ደንብ ተከትሎ ፈቃድ ከሚሰጥ አካል አስፈቅዶ መያዝና መጠቀም ሲገባ ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ሳያስፈቅድ የመኖሪያ ቤቱ በ21/12/2005 ዓ.ም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ብርበራ በተካሄደበት ወቅት፡-
1ኛ/ የውግ ቁጥር 473955 የሆነ ታጣፊ ክላሽ ጠመንጃ፣ 2ኛ/ የውግ ቁጥር 2306 የሆነ ባለ ሰደፍ ክላሽ ጠመንጃ፣
3ኛ/ የውግ ቁጥር ኤፍ.ኤ 990 የሆነ ኡዚ ጠመንጃ 4ኛ የውግ ቁጥር 22009411 እስታር ሽጉጥ፣
5ኛ/ አንድ የጭስ ቦምብ ከነፊውዙ እና 6ኛ/ በርካታ የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ
በፈፀመው እንዲይዝ ያልተፈቀደለትና ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል።
92ኛ ክስ በ24ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 419/1/ሀ/ እና /ለ/ ላይ የተደነገገውን መተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከግንቦት ወር 1983 ዓ.ም ጀምሮ መስሪያ ቤቱን እስከለቀቀበት የካቲት ወር 2005 ዓ.ም ድረስ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ደህንነት ሰራተኛ በኋላም አማካሪ ሆኖ ሲሰራ ከብር 1600 /አንድ ሺ ስድስት መቶ ብር/ እስከ ብር 6000 /ስድስት ሺህ ብር/ ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው የነበረ ሲሆን ከዚሁ ህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን፤ በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 17 ቀበሌ 25 ክልል ውስጥ በካርታ ቁጥር ሊዝ ዕጣ 8155/94 በኖርቴክ ቁጥር 992478 በተሰጠው 175 ካ.ሜትር ቦታ ላይ የገቢ ምንጩ ሊያሰራው የማይችለውን ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ G+3 ዘመናዊ ህንፃ ቤት ሰርቶ በወር 50 ሺ ብር እያከራየ በመገኘቱ በፈፀመው ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
93ኛ ክስ በ24ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 407/1/ሀ/ እና /2/ ላይ የተመለከተውን መተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ደህንነት ኃላፊ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት የተሰጠውን የስራ ሀላፊነትና ስልጣን በግልፅ ተግባር አላግባብ በመገልገል በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት በማድረስ የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት በማሰብ፣ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 17 ቀበሌ 25 ክልል ውስጥ በርካታ ቁጥር ሊዝ ዕጣ 8155/94 በኖርቴክ ቁጥር 992478 175 ካ.ሜትር ቦታ በህጋዊ መንገድ ተሰጥቶት እያለ በዚሁ ቦታ ላይ ቤት ለመስራት ፕላንና የግንባታ ፍቃድ ወስዶ በሚሰራበት ወቅት ከ1996 እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ስልጣኑን ተገን አድርጎ ከተሰጠው ቦታ ጎን የሚገኘውንና የሊዝ ግምቱ 2,923,267.50 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከ50/100/ የሆነ 375 ካ.ሜትር የመንግስት ቦታ አጥሮ በመያዝ ቤት የገነባበት በመሆኑ በፈፀመው በስልጣን አለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል።¾
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ኦክቶበር 23 ዕትም