Tuesday, October 15, 2013

‘በመልሱ ጨዋታ እናሸንፋለን…ጀርመንን መግጠም አለብን!’ ሰዉነት ቢሻዉ



አዲስ አበባ ዛሬ ጻጥ ረጭ ብላ ዉላለች፤ትላንት የቡድኑን ማልያ ያለበሰ ሰዉ ትራፊክ አልያም ፖሊስ ብቻ ነበር፤ዛሬ ግን አንዳንዶች ብቻ ነበሩ መለያዉን የለበሱት..ስሜቶቹ ተንፈስ ያሉ ይመስላል፤
ትላንት ከጨዋተዉ ቡሁዋላ ስቲፈን ኬሺ አስተያየት ሰጥቶ ነበር፤አሰልጣኝ ሰዉነት ግን መግለጫ ሳይሰጡ ነበር ከስታድየም የወጡት..ዛሬ ረፋድ ላይ በሬድዮ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፤
ትላንት ተጫዉተን ለማሸነፍ ነበር ያሰብነዉ ግን አልተሳካልንም፤ሁሌም ተጫዉተህ ማሸነፍ አትችልም፤ለቻን ዉድድር ሳንጫወት ተበልጠን ነበር በእድል ያለፍነዉ፤ትላንት ግን ተሸንፈናል ብለዋል፤
የአዳነ ግርማን መቀየር በተመለከተ..እሱ እንደደከመ ስላመንኩኝ ነዉ የቀየርኩት..በዚህ ቡድን ማንም ይቀየራል፤ኳሶችን መቀማት ጀምሮ ነበር፤አንዳንድ ሚድያዎችም ለምን ወጣ ሲሉ ሰምቻለሁ፤እኔ ያሰብኩት ነገር ናይጄሪያዎች ላይ ብዙ ማግባት አለብን ብዬ አጥቂ ባህሪ ያለዉን ኡመድን ያስገባሁት…ኡመድ በኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ልምድ አለዉ!!እናም ለማግባት በማስብ ነዉ ብለዋል፤
ለቀጣዩ ጨዋታ ለማሸነፍ እድል እንዳለም አሰልጣኙ ተናግረዋል፤እንዲህ በማለት..
አትጠራጠር እነዚህ ልጆች…እነ አዳነ እና ደጉ በመልሱ ጫዋታ ኮከብ እንደሚሆኑ!!ምንም አይከብደንም..ናይጄሪያን እዚህ እንደተጫወትነዉ አድርገን 2-0 አልያም 2-1 ማሸነፍ አያቅተንም፤የወዳጅነት ጨዋታ ያስፈልገናል፤ናይጄሪያ ከጣሊያን ጋር ይጫወታል፤እኛም ደግሞ ከጀርመን ጋር መጫወት አለብን..ኬንያ ምናምን መባል የለበትም፤ለቡድናችን ቀላል ግምት መሰጠት የለበትም!!!
ናይጄሪያ እንደዛ የተወራለትን ቡድን በልጠን አሳይተናል..እንደዛ የተጋነነ ቡድንን በልጠናል!!…
አሰልጣኙ የሰጡት አስተያየት ቀደም ሲል ከጨዋታዉ በፊት ከሰጡት ጋር በአብዛኛዉ የሚጋጭ ነዉ፤የወዳጅነት ጨዋታ አለመኖሩ ምንም ተጽእኖ የለዉም ብለዉ ነበር አሁን ደሞ ከትልልቅ ቡድን ጋር እናድርግ ብለዉ ጀርመንን መርጠዋል
ተጫዉቶ ማሸነፍ አለብን ብለዋል አሁን…ቀደም ብለዉ ግን በምንም መንገድ ለማሸነፍ እንደሚጫወቱ..ተጫዉቶ ማሸነፍ ሳይሆን የተጋጣሚ ቡድንን አጨዋወት አይተዉ እንደሚወስኑ (ካጠቃ ሊከላከሉ ከተከላከለ ሊያጠቁ) እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጸዋል፤እስከትላንት ድረስ የነበረዉ ዋልያም በመጫወት ሳይሆን በመጠለዝ ጊዜ ይጨርስ እንደነበር ታይትዋል፤
ተጫዉቶ ማሸነፍ የሚመርጥ አሰልጣኝ ለመጫወት የሚሆኑ ፈጣሪ ተጫዋቾችን ይይዛል፤በተለይ መሀል ሜዳ ላይ..የአሁኑ ዋልያ ግን ትላንት ካስገባቸዉ 4ት አማካዮች እንኳን አንዱም ደምበኛ አማካይ (ለመጫወት ኳስ በመያዝ እና ቡድን በመምራት)አይደለም፤አዳነ በክለቡ አጥቂ..አስራት እና አዲስ ነጣቂ..ምንያህል የክንፍ ተጫዋቾች ናቸዉ!!
ለትላንቱ የዋልያ የመጀመሪያ 45ት ደቂቃ ቅብብል መሰረቱ አዳነ ነበር፤ደፍሮ ከተከላካዮች ለመቀበል ሞክርዋል፤አደራጅትዋል..ግን ከመሀል ሜዳ በሁዋላ የነበረዉ ቅንብር ደካማ ነበር፤ያም ቢሆን ግን ለመጫወት ከታሰበ እንዴት ዋነኛዉን ተጫዋች በ65 ደቂቃ ከቡድኑ እንዲወጣ ይደረጋል!!
ትላንት መላዉ ሀገሪቱ በዋልያዉ ተነቃንቃለች፤የቡድኑ ጥንካሬ እና ድክመት እንዲሁም መጫወት ስላለበት አጨዋወት ብዙም ሳይባል ጨዋተዉ ተጀምሮ እንደዛ አልቅዋል፤አሁንም ካላባር-ናይጄሪያ ላይ እናሸንፋለን ማለት አሁንም የህዝቡን ስሜት ያለማገናዘብ መስቀል ተገቢ አይሆንም!!
አስኪ እነዚህን ነጥቦች እንወያይባቸዉ!!

 http://www.ethiotube.net

No comments:

Post a Comment