ለካላባሩ የመልስ ጨዋታ ዝግጅቱ ሰኞ ተጀምርዋል፤በአዲስ አበባ ስታድየም ነዉ ዝግጀቱ…ሰኞ 4ት የሳንጆርጅ
ተጫዋቾ መጥተዉ ከሌሎቹ ጋሩ ቀላል ልምምድ ሰሩ፤የተቀሩት እሁድ ስለተጫወቱ እረፍት ላይ ነበሩ፤ትላንት በተካሄደዉ
ልምምድ 2ት ተጫዋቾች አልተገኙም ነበር፤አዳነ ግርማ እና አይናለም ሀይሉ ጉንፋን ስላጠቃቸዉ ነዉ ከልምምድ
የቀሩት..አይናለም ጉንፋን ብቻ ሳይሆን የሆድ ህመምም አጋጥሞታል፤ሌላዉ ዛሬ በልምምድ ሜዳ ያልነበረዉ ምንያህል
ተሾመ ነዉ ፤አሱም በእሁዱ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመዉ ተነግርዋል፤ነገር ግን ጉዳቱ ለክፋ ስለማይሰጥ ከነገ
ወዲያ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል፤
በዋልያዉ ዙሪያ ሌላዉ አዲስ ነገር በስዩም ተስፋዬ(በ2ት ቢጫ ምክንያት አራፊ ነዉ) ቦታ ተተኪ የማግኘቱ ጉዳይ
ነዉ፤እስካሁን ድረስ በቦታዉ ቢያድግልኝ ኤልያስ…አሉላ ግርማ… በተለያየ ጊዜ በቦታዉ ተጫዉተዋል፤አሉላ በናይጄሪያዉ
ስብስብ ዉስጥ አለነበረም፤ከጉዳት መልስ በጥሎ ማለፍ ፍጻሜ ተጫዉትዋል፤እናም አሁን በአሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ጥሪ
እንደሚደረግለት ተሰምትዋል፤ከነገ በጉዋላ ባሉት ቀናትም ይፋ ይሆናል፤ሳላሀዲን ባርጌቶ በዚህ ቦታ ለአሰልጣኝ ሰዉነት
ቡድን እንደ ሌላ አማራጭ ነዉ፤
ዳያስፖራዎቹ ተጫዋቾች..አሚና አስካር እና ዋሊድ አታም የዋልያዎቹ የቤት ስራ ሁነዋል፤የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ
የቴከተኒክ ክፍል ልጆቹን ለማምጣት ጥረት እያደረገ ነዉ፤በተለይም ዋሊድ አታን በተመለከት ተጫዋቹን በስልክ ከማናገር
እስከ ድብዳቤ ልዉዉጥ ድረስ ቴክኒክ ክፍሉ ተንቀሳቅስዋል፤አሚን አስካርንም ለመልሱ ጨዋታ ላመድረስ እንዲሁ ጥረቶች
ቀጥለዋል፤ነገር ግን አሰልጣኝ ሰዉነት ተጫዋቾቹን ይፈልጉ አይፈልጉ በይፋ አልተናገሩም፤በፌዴሬሽኑ በኩል ጉዳያቸዉ
እንዲታይ ከማለታቸዉ ዉጭ በቅርብ ጊዜ ፍቃድ ይሁን ተቃዉሞ አላሰሙም፤
የወዳጅነት ጨዋታን በመለከተ 2ት ቡድኖችን ለመግጠም ሙከራዎች እየተደረጉ ነዉ፤ሁለቱም የምእራብ አፍሪካ ሀገራት
ናቸዉ፤በደቡብ አፍሪካ ያሸነፈችን ቡርኪና ፋሶ እና ካሜሮን ናቸዉ፤አዲሱ ፌዴሬሽን እንደቀድሞዉ አዉርቶ ጨዋታዎቹ
ከሚቀሩ አረጋግጦ ማሳወቅን መርጥዋል፤
ለማንኛዉም የካላባሩ ተጠባቂ ጨዋታ 22ቀናት ብቻ ቀርተዉታል፤
http://www.ethiotube.net
No comments:
Post a Comment