ከአቡጃ ደጋፊዎች ይመጣሉ ሲባል ሰማንና ገረመን ካላችሁ ተሸዉዳችሁዋል…እነሱ እኮ በአይሮፕላን ለዛዉም የሀገሪቱ መሪ ከፍሎላቸዉ ነዉ የሚመጡት…
የአዳማዎች/ናዝሬቶቹ የዋልያ ደጋፊዎች ግነ ለዋልያዉ ክብር ሲሉ 100ኪ.ሜትር በእግር ተጉዘዉ አዲስ አበባ
ለመግባት ጉዞ ጀምረዋል፤ትላንት የተጀመረዉ ጉዞ ዛሬ ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት ላይ ደርስዋል፤ደጋፎዎቹ 50አከባቢ
ይሆናሉ፤ታሪካዊዉን ጨዋታ በታሪካዊ መንገድ ለማየት በሚል ነዉ፤ጥቂቶቹ እንስቶች ሲሆኑ አብዛኞቹ ወንዶች ናቸዉ፤
ደጋፊወቹ ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት ሲገቡ ለከተማዉ ህዝብ ግርምትን ጭረዋል፤50ኪሎ ሜትሩን ለመጨረስ ከግማሽ ቀን
በላይ ወስዶባቸዋል፤ዛሬ እዛ አድረዉ ነገ አዲስ አበባ ለመግባት አቅደዋል፤ከዛ ደሞ የሌሊቱን ወረፋ በስታድየም ዙሪያ
አሳልፈዉ ወሳኝዋን ቀን በስታድየም ለዋልያዎቹ ድጋፍ ለመስጠት ስንቃቸዉን አዘጋጅተዋል፤
ዛሬ ያረፉበት ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት ከተማ ደደቢት እና ቡና የቅድመ ዉድድር ዘመን ልምምድ እያካሄዱ
ነዉ፤የክለቦቹ ተጫዋቾች በደጋፊዎቹ ተገርመዋል፤በተለይ መስኡድ መሀመድ የተባለዉ የዋልያዉ የቀድሞ አማካይ በደጋፊዎቹ
መቅናቱን ጭምር ነግሮኛል፤
“እኛ እንኳን ጨዋታዉን በስታድየም ለማየት አልታደልንም፤እነሱ በእግራቸዉ ይህንን ሁላ መንገድ አቋርጠዉ
መሄዳቸዉ ከዛም በአይናቸዉ ጨዋታዉን መመልከታቸዉ ያስቀናል…እኛም እነሱን እያሰብን ጨዋታዉን በቴሌቪዝን
እናያለን”ብሎኛል!!
ተጓዥ የዋልያዉ ደጋፊዎች ከፊት ለፊታቸዉ ትልቅ ባነር ይዘዉ ነበር ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት የገቡት…”ከስምጥ ሸለቆዋ እንቁ አዳማ/ናዝሬት የመጡ የዋልያ ደጋፊዎች”የሚል!!
ይህንን ነገር ስሰማ በርግጥም ለደጋፊዉ ሲባል እንኳን ዋልያዉ በአዲስ አበባ ቢያሸንፍ የሚል ሀሳብ
ተናነቀኝ!!ኮሊንስ የተባለ ጋዜጠኛ የአዲስ አበባ ስታድየም አይነት ጩሀት ያለበት ስታድየም አይቼ አላቅም ሲል ክፉኛ
ገርሞኝ ነበር፤ምክንያቱም ስታድ ደ ሀይለ ስላሴ በአፍሪካ እምብዛም ከማይጮህባቸዉ ስታድየሞች አንዱ እንደሆነ በስራ
አጋጣሚ ተመልከቻለሁና!!ይህ ደጋፊ ግን በጩሀት ድጋፉ ሳይሆን በዋናነት ለሀገሩ እግር ኳስ ቡድን ባለዉ ጥልቅ
ፍቅር የሚገለጽ ነዉ!!ሰዎቹ ሸገር እንደገቡ አናግሬ ቃላቸዉን አመጣላችሁዋለሁ!!!ማን እንደ ስምጥ ሸለቆዋ
እንቁ???!!!
http://www.ethiotube.net
No comments:
Post a Comment