በእንግሊዘኛው ምህፃር FRONTEX የተባለው ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የድንበር ጥበቃ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ፣
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን በመመለስ የደረሰበትን ወቀሳ አመነ ።
ድርጅቱ ለአንድ የጀርመን ቴሌቬዥን በሰጠው ቃለ ምልልስ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ስደተኞች ወደ ሶስተኛ ሃገራት በኃይል
እንዲመለሱ መደረጉን አምኗል ። ለስደተኞች መብት የሚከራከሩ ድርጅቶች FRONTEX የፈፀመው ተግባር ዓለም ዓቀፍ
የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን የሚፃረር ነው ሲሉ ይከሳሉ ። ሂሩት መለሰ ።
እጎአ በ2004 የተቋቋመው FRONTEX ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ድንበር ጥበቃ እገዛ የሚያደርግ ድርጅት ነው
። ይኽው ድርጅት በአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብቶች ህግጋት መሠረት የህብረቱ አባል ሃገራት የድንበር አስተዳደር
መስራቱን የሚከታተልና የሚያስተባብር መስሪያ ቤት ነው ።
ይሁንና የስደተኞች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ የስደተኞችን መብት ይጥሳል ፤
ስደተኞቹንም ለአደጋ ያጋልጣል ። ድርጅቱን በዚህ ከሚወቅሱት የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውስጥ አባሻ ኤጀንሲ
የተባለው ለስደተኞች እርዳታ የሚሰጥ ግብረሰናይ ድርጅት ይገኝበታል ። የአባሻ ኤጀንሲ ሃላፊ አባ ሙሴ ዘርዓይ
ድርጅታው ፍሪሮንቴክስን የሚወቅብስበትን ምክንያት ያብራራሉ ።
ከዚያ ይልቅ እንደ አባ ሙሴ ፍሮንቴክስ በሰብዓዊነት የስደተኞች ህይወት ለመታደግ ቅድሚያ መስጠት ነበረበት ።
ፍሮንቴክስ ከአንድ ዓመት በፊት ስደተኞች ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር እንዲመለሱ በማድረግ ሂደት ኃይል በመጠቀሙ
የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት እርምጃው ኢሰብዓዊ ነው ሲል ብይን አሳልፎበት ነበር ። ይሁንና ምግባሩ
አለመቆሙን ARD የተባለው የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያ ባደረገው ምርመራ ደርሶበታል ። በዚሁ ጉዳይ ላይ ለቴሌቪዥን
ጣቢያው ቃለ ምልልስ የሰጡት የድርጅቱ ሃላፊ ኢካ ላይቲነን ስደተኞችን በኃይል ወደ መጡበት እንዲመለሱ ማድረግ
ተቀባይነት እንደሌለው ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል ።
ሃላፊዋ የፍሮንቴክስ የሥራ ባልደረቦችም ስደተኞችን ጠርዞ ወደ ሶስተኛ ሃገራት በመላክ ተሳትፈውበታል የሚባለውንም
በአንዳንድ ሁኔታዎች አልተደረገም ለማለት አይቻልም ሲሉ አምነዋል ። በቅርቡ በኢጣልያዋ የላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ
ወደ 364 የሚደርሱ ስደተኞች ህይወት ከጠፋበት የጀልባ መስጠም አደጋ በኋላ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የሃገር
ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ ፍሮንቴክስን ለማጠናከር ተስማምተዋል ። አባ ሙሴ ፍሮንቴክስ የሚጠናከረው
ስደተኞችን ወደ መጡበት ለመመለስ መሆን የለበትም ይላሉ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ
dw.de
No comments:
Post a Comment