ጌታነህ ከበደ በእሁዱ ጨዋታ አይሰለፍም
ምክትል አሰልጣኙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ ለደቡብ አፍሪካው ቢድ ቪስት ዊትስ የሚጫወተው ጌታነህ ከበደ ለክለቡ ሲጫወት ካጋጠመው ጉዳት ባለማገገሙ ነው በጨዋታው የማይሰለፈው ።
ጌታነህ በመብራት ሀይል ሜዳ ልምምዱን እያደረገ የሚገኘውን ብሄራዊ ቡድን ለመቀላቀል ዛሬ በስፍራው ቢገኝም በህመም ምክንያት ዋልያዎቹን መቀላቀል አልቻለም ።
በውጭ ሀገራት ለተለያዩ ክለቦች እየተጫወቱ የሚገኙት አዲስ ህንጻ ፣ ሽመልስ በቀለ እና ሳላሃዲን ሰኢድ ግን ብሄራዊ ቡድኑን ተቀላቅለው ልምምድ የጀመሩ ሲሆን ፥ በእሁዱ ወሳኝ ጨዋታም የሚሰለፉ ይሆናል ።
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሳላሃን ሰዒድ በእሁዱ ጨዋታ አይሰለፍም በሚል የወጣው ዜናም ከእውነት የራቀ መሆኑን ምክትል አሰልጣኙ አረጋግጠዋል ።
https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/09/3412/
No comments:
Post a Comment