Saturday, October 5, 2013

የትውልደ ኢትዮጵያዊው አሚን አስካር ጥያቄ ተቀባይነት ሊያገኝ ይችላል - አሰልጣኝ ሰውነት Coach Sewnet: It is possible for Amin Askar to play for Team Ethiopia.


Coach Sewnet: It is possible for Amin Askar to play

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሚን አስካር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫዎት እንደሚፈልግ ገለጸ።
በኖርዌይ ሊግ ብራን ክለብ የተሳካ ጊዜን እያሳለፍ የሚገኘው አሚን አስካር በአሰልጣኝ ሰውነት ቡድን ውስጥ በመካተት የትውልድ ሃገሩን መርዳት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አስካር ለትውልድ ሃገሩ ለመጫዎት ያለውን ፍላጎት ከሱፐር ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።
’’የእኔ ህልም የትውልድ ሀገሬን ወክየ እግር ኳስን በአለም አቀፍ ደረጃ በብቃት መጫወት ነው” ያለው አስካር ፣ በአውሮፓ በተጨዋችነት ያሰለፋቸው 11 ዓመታት ለትውልድ ሃገሩ ጠቃሚ ልምድ እንደሚያስገኙለት እምነቱን ገልጿል ።
በኖርዌይ የወጣቶች ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ መጫወቱን የገለጸው ኦስካር ፣ ሀገሩን የመርዳት ፍላጎቱን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ይመለከቱታል ብዬ አምናለሁም ብሏል፡፡
በሚያሳልፈው ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱ ደስተኛ መሆኑን የሚናገረው አስካር ፣ ከትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ጋር ወደ ዓለም ዋንጫው ማቅናት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
የመስመር ተጫዋቹ አስካር በሚጫወትበት ሊግ ባለፈው አመት የአመቱን ምርጥ ግብ ሽልማት አሸንፏል።
የ28 ዓመቱ አስካር በሃረር ተፈሪ በር አካባቢ ተወልዶ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኖርዌይ በማቅናት ኑሮውን በዚያው ሃገር አድርጓል።
በሌላ በኩል አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቡድናቸውን መቀላቀል የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ አሳማኝ ብቃት እስካሳየ ድረስ መቀላቀል እንደሚችል ተናግረዋል።
አሰልጣኙ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ፥ ለአስካርም ሆነ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ብቃቱ እስካላቸው ድረስ በራቸው ክፍት መሆኑን ነው የሚናገሩት።
አስካርን በተመለከተም ኢትዮጵያዊነቱ ከተረጋገጠ እና በልምምድ ወቅት ለቡድኑ የሚመጥን ብቃት ካሳየ ቡድኑን ሊቀላቀል ይችላል ብለዋል።
አሰልጣኝ ሰውነት የልጁን ዜግነት ማጣራቱ እና የፓስፖርት ጉዳይ ጊዜ ስለሚወስድ ፤ አስካር ለጥቅምት ሶስቱ ጨዋታ ቡድኑን ይቀላቀላል የሚል እምነት እንደሌላቸውም ነው የተናገሩት።
አያይዘውም የአርሰናሉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ጌዲዮን ዘላለም ለቡድኑ ጥያቄ ካቀረበም ጉዳዩን እንደሚያጤኑት ገልጸዋል።

sodere

No comments:

Post a Comment